፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 19 2016| NBC ETHIOPIA-ከመጪው ግንቦት 21 እስከ 27 በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉ እንደሚጀመር ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በሂደቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶችና ተፈናቃዮችን ጨምሮ 11 የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
በእዚህም ከ2500 በላይ ተወካዮች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተነግሯል።
የምክክሩ ተሳታፊዎችን የመምረጥ ሂደቱ ጊዜ መፍጀቱን የገለፀው ኮሚሽኑ በቀረው ጊዜ ስራውን ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
በ-መቅደስ ደምስ












