፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 14 2016| NBC ETHIOPIA- በሳይንስ ሙዚየም በመካሄድ ላይ በሚገኘው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ ጎን ለጎን በዲጂታል ኢኮኖሚ ዙርያ የፓናል ውይይት ተካሄደ ።
ስትራይድ ኢትዮጵያ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ተጨማሪ አቅምና እውቀት በመፍጠር የኢኮኖሚ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል።

በመድረኩ የዲጂታል 2025 ኢትዮጵያ ስትራቴጂ መጽደቅ በርካታ ውጤቶችን እያመጣ ነው የተባለ ሲሆን፡፡
ባለፉት ሶስት ዓመታትም የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታን የሚያፋጥኑ አውታሮች በስፋት ወደ ስራ ገብተዋል ተብሏል።
በስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ የቀረቡ ስራዎች ኢትዮጵያ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ትልቅ የለውጥ እርምጃ ላይ መሆኗን የሚያመላክት መሆኑ ተነስቷል።

ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ በርካታ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ተቋማትን እያሳተፈ ይገኛል፡፡
የስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በይፋ መከፈቱ ይታወቃል።
ዓመታዊው ኤክስፖ “ሳይንስ በር ይከፍታል ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል” በሚል መሪ ሃሳብ በሳይንስ ሙዚየም እስከ ግንቦት 18 2016 ዓ.ም ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
በ-ሰብለ ወንድማገኝ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












