፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 13 2016| NBC ETHIOPIA-ዴቪድ ሌተርማን ለረጅም አመታት አየር ላይ የቆየን የቴሌቪዥን ሾዎ በመምራት በአለም አቀፍ ደረጃ ስሙ ይነሳል፡፡
ዴቪድ ሌተርማን ሌት ናይት ሾው የተሰኘውን ፕሮግራም በመራባቸው አመታት ከአስራ ዘጠኝ ሺህ በላይ እንግዶችን አስተናግዷል፡፡
ሌተርማን የፕሮግራም መሪ ብቻ ሳይሆን ፕሮዲዩሰር በተጨማሪም ኮሜዲያን ሲሆን ውልደቱ በአውሮፓውያኖቹ አቆጣጠር ጥቅምት 12 1947 ኢንዲያና በተባለች የአሜሪካ ግዛት ነው፡፡
ከቦል ስቴት ዩኒቨርሲቲ በ1969 በቴሌኮሙኒኬሽን የተመረቀ ሲሆን የሚዲያ ህይወቱ የጀመረው ለአንድ ሳምንት በዘለቀው የቦል ስቴት የሬዲዮ ፕሮግራም ነው።

ሌተርማን በፈረንጆቹ ከ1970 እስከ 1974 ባሉት አመታት ውስጥ የአየር ሁኔታ ባለሙያና የቲቪ አስተዋዋቂ በመሆን አገልግሏል፡፡
ዴቪድ ወደ ቴሌቪዥን ሾው መሪነት የመጣው በ1982 ሲሆን “Late Night with David Letterman” የተሰኘውን ፕሮግራም እስከ 1993 በNBC ቴሌቪዥን በፕሮግራም መሪነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡
የፕሮግራም መሪነቱን መቀጠል እንደማይችል ለጣቢያው ስራ አስፈጻሚዎች ያሳወቀው ዴቪድ ስራ አስፈጻሚዎቹ ይህንን ሲሰሙ በሱ ምትክ ሌላ የፕሮግራም መሪን ማፈላለግ ጀመሩ፡፡
በስተመጨረሻም ጄይ ሌኖን የዴቪድ ሌተርማን ምትክ አድርገው መረጡ፡፡
11 አመታት ከሰራበት ኤን ቢሲ ቴሌቪዥን በ1993 ወደ ሲቢኤስ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከወጣ በኋላ ጡረታ እስከ ወጣበት 2015 ድረስም “Late Show with David Letterman” የተሰኘውን ፕሮግራም ሲመራ ቆይቷል፡፡
አዲሱ “Late Show with David Letterman” የተሰኘው ሾው ለ22 አመታት ከቆየ በኋላ ለ33 አመታት በቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የነበረውን ቆይታ በማጠናቀቀ ጡረታ መውጣቱን ይፋ አደረገ፡፡
በ 2014 ሌተርማን በሚቀጥለው ዓመት ጡረታ እንደሚወጣ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ እስጢፋኖስ ኮልበርት እንደሚተካ ተገለጸ።
ሌት ናይት ከዴቪድ ሌተርማን ጋር የተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አምስት የኤሚ ሽልማቶችን ሲያገኝ ለ35 ጊዜያትም እጩ መሆን ችሏል፡፡

ዴቪድ ሌተርማን 33 አመታት የዘለቀውን የቴቪ ሾው መሪነት የደመደመው ግንቦት 20፣ 2015 በትላንትናው እለት ነበር፡፡
ሌተርማን አንዳንድ ታዋቂ ግለሰቦች ላይ ተቃውሞን በመሰንዘርም ይታወቃል፡፡
ታዋቂው የቲቪ ፕሮግራም አዘጋጅ የፈረንጆቹን ሚሊኒየም ያከበረው በድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት በሆስፒታል ነበር፡፡
ኦፕራ ዊንፍሬይ፣ ጆርጅ ክሎኒ፣ ጁሊያ ሮበርትስ፣ ስቲቭ ማርቲን፣ ዶን ሪክልስ፣ ጆን ትራቮልታ፣ ቶም ሀንክስ የመሳሰሉ ግለሰቦች ከዴቪድ ሌተርማን የመጨረሻ እንግዶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
እንደ አውሮፓውያኖቹ ከየካቲት 1 ቀን 1982 ጀምሮ እስከ 2015 ለሰላሳ ሶስት አመታት የቆየው የዴቪድ ሌተርማን ከቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅነት ጡረታ የወጣው በ2015 ሲሆን ግንቦት 20 2015 በትላንትናው እለት ደግሞ የመጨረሻ ቃለ መጠይቁን የሰራበት እለት ነው፡፡












