Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የኢየሱስ ክርስቶስ ፊልም

May 4, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

ዓለም ላይ በየጊዜው በርካታ ሀይማኖታዊ መልዕክትን ያዘሉ ፊልሞች እና ተከታታይ ድራማዎች ይሰራሉ።እነዚህ ፊልሞች በሀይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ ተወዳጅ ሲሆኑ ስለ ሀይማኖቱም ቢሆን ጥሩ ማስተማሪያ ናቸው። ሀይማኖታዊ ይዘቶችን በማስመልከት ጥልቅ የሆነ ትምህርት እና መልዕክት ያስተላልፋሉ።

ነገ እሁድ በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የትንሳኤ በአል ምክንያት በማድረግ በዓለማችን ላይ የተሰሩ የኢየሱስ ክርስቶስን ከልደቱ እስከ ትንሳኤው ያለውን የህይወት ታሪክ የሚያስመለክቱ ፊልሞችን በጥቂቱ እናስቃኛችሁ።

1, From the Manger to the Cross በቅድሚያ የምናገኘው በ ጂን ጋውንቲ ተጽፎ በሲድኒ ኦልኮት ዳይሬክት የተደረገው From the Manger to the Cross የተሰኘውን ፊልም ነው። እ.ኤ.አ በ1912 የተለቀቀው ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ  ፊልም ድምፅ አልባ ፊልም ሲሆን በካለም ኩባንያ ተዘጋጅቷል።

ፊልሙም የተቀረፀው በግብፅ እና በፍልስጤም ሲሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጋር በማሰናሰን ይተርካል። በትወና አሜሪካዊው ሮበርት ሄንደርሰን ተሳትፎበታል።  

ፊልሙ በአጠቃላይ የ70 ደቂቃ ርዝማኔ ሲኖረው የኢየሱስ ክርስቶስን  ልደት፣ የደቀ መዛሙርት ጥሪን፣ የተራራው ስብከትን፣ የዓይነ ስውራን ፈወስ፣ የአልዓዛርን ትንሣኤ፣ የመጨረሻው እራትን፣ ስቅለት እና ትንሣኤን ያሉ ትዕይንቶችን ያስመለክተናል፡፡ይህ  የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት ፊልም በቀጣይ ለተሰሩ ሀይማኖታዊ ፊልሞች ትልቅ ምዕራፍ ከፋች ነበር፡፡

2, The Life of Christ (1952)

ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ፊልም እ.ኤ.አ በ1952 የተሰራ ነው፡፡ The Life of Christ ይሰኛል፡፡  በአይርቪንግ ፒሼል ዳይሬክት የተደረገ ፊልም ነው። አዲስ ኪዳን ላይ ተመሰርቶ የተሰራው ይህ የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት የሚያሳይ ፊልም በብዙ የሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ ተወዳጅነትን አግኝቷል፡፡

ፊልሙ የኢየሱስ ክርስቶስ  ውልደቱን ፣ በልጅነቱ እና በመጨረሻ በአዋቂነት አገልግሎቱን ይተርካል።  የተራራውን ስብከት ፣ የመጨረሻውን እራት ጨምሮ ተአምራቶቹን፣ ምሳሌዎችን እና ትምህርቶቹን ይዳስሳል።

ፊልሙ ፋሚሊ ቲያትር ፕሮዳክሽንስ በተሰኘ የካቶሊክ ፊልም ሰሪ ድርጅት የተሰራ ነው፡፡ ጄፍሪ ሀንተር የኢየሱስ ክርስቶስን መስሎ ተጫውቷል።

3, Jesus of Nazareth (1977)

“የናዝሬቱ ኢየሱስ” የተሰኘው ፊልም እ.ኤ.አ በ1977 የተሰራ የሲሆን ለእይታ የበቃው በፍራንኮ ዘፊሬሊ ዳይሬክት ተደርጎ በአንቶኒ በርጌስ እና በሱሶ ሴቺ ዲ አሚኮ ተፃፏል። ይህ ፊልምም የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት ከቤተልሔም ልደቱ እስከ ስቅለቱና ትንሣኤው ድረስ ይተርካል።

“የናዝሬቱ ኢየሱስ” በተመልካቾች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ  እና  ከስድስት ሰአታት በላይ የሚዘልቅ ፊልም ነው።

ፊልሙ እምነትን፣ ርህራሄን፣ ቸርነትን እና በኢየሱስ እና በዘመኑ በነበሩት መሪዎች መካከል የነበረውን ግጭት ጨምሮ የተራራውን ስብከት፣ የመጨረሻው እራት እና ስቅለቱን ያሳያል።

4, The Jesus Film (1979)

The Jesus Film  የተለቀቀው እ.ኤ.አ  በ1979  ነው። ይህ ፊልም ከመጽሐፍ ቅዱስ በሉቃስ ወንጌል ላይ የተመሠረተ ነው። ፊልሙ የተሰራው በካምፓስ ክሩሴድ ፎር ክርስቶስ  እና በፒተር ሳይክስ ሲሆን በጆን ሄይማን ዳይሬክት ተደርጓል።

ፊልሙ የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት፣ ሕይወት፣ ትምህርት፣ ሞት እና ትንሣኤ ያሳያል። ፊልሙ የኢየሱስ ክርስቶስን ምድራዊ ቆይታ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምዕራፎች በማጣቀስ ለብዙ ተመልካቾች መድረስ ችሏል፡፡

ፊልሙ የተቀረፀው እስራኤል ሲሆን ፊልሙም የተሰራው በኢየሱስ ዘመን ይነገር በነበረው የአረማይክ ቋንቋ ነው።

5, The Passion Of The Christ

በዝነኛው የሆሊውድ ተዋናይ፥ ደራሲና ዳይሬክተር ሜል ጊብሰን ተፅፎ የተዘጋጀና ፕሮዲዩስ የተደረገ ፊልም ነው። ፊልሙ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻዎቹ አስራ ሁለት የስቃይና የስቅላት ሰዓታት ላይ አተኩሮ ተሰርቷል።

የኢየሱስ ክርስቶስን ህይወት መሰረት አድርገው ከተሰሩት ቀደምት የሆሊውድ ፊልሞች በተለየ ሁኔታ The Passion Of The Christ የክርስቶስን እውነተኛ ስቃይ በተሻለ ሁኔታ አቅርቦ ስለመሰራቱ ብዙዎች መስክረውለታል፡፡

የፊልሙ ቋንቋንም በወቅቱ የነበረውን፥ ጥንታዊውን “አርማይክ” ቋንቋን ተጠቅሟል።ፊልሙም አጠቃላይም 30 ሚልዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል።

በ-ሀይማኖት ወርቁ

Tags: chirst filmchristfilmJesuses
ShareTweetShare
Previous Post

የኔቶ ወታደሮች ወደ ዩክሬን መሄድ የለባቸውም

Next Post

አሜሪካ ከጦርነት ትርፍ ፈላጊ ናት 

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
አሜሪካ ከጦርነት ትርፍ ፈላጊ ናት 

አሜሪካ ከጦርነት ትርፍ ፈላጊ ናት 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች መኖሪያ ቤቶች ሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች መኖሪያ ቤቶች ሰጠ

በእስራኤል የሚገኙ ኃይማኖታዊ ስፍራዎች

በእስራኤል የሚገኙ ኃይማኖታዊ ስፍራዎች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?