፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 26 2016| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስተላለፈ
አስተዳደሩ በሰው ተኮር ስራው አሳሳቢውን የቤት ችግር ለመቅረፍ በሚያደርገው ስራ በወራቶች ግንባታቸው የተጠናቀቀ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለነዋሪዎች አስተላልፏል።
በከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና ከባለሃብቶች በተሰበሰበ ገንዘብ በአዲስ ከተማ እና አራዳ ክፍለ ከተሞች የተገነቡትን መኖሪያ ቤቶች ከንቲባ አዳነች አበቤ ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል።

በመዲናዋ የተጎሳቆሉ መኖሪያ ቤቶችን የማፍረሱ ስራ ከተማዋን በሚመጥኑ መሰል መኖሪያ ቤቶች ለመተካት ያለመ መሆኑን ከንቲባዋ ገልፀዋል።
በመንግስት ጥረት ብቻ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል የገለፁት ከንቲባዋ በባለሃብቶች ትብብር እየተሰራ ያለው መሰል ተግባር ሊበረታታ ይገባል ብለዋለ። በቤት ግንባታው የተሳተፉ አካላትን አመስግነው ለቀጣይ ስራዎች ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ግንባታውን ለደገፉ ባለሃብቶች የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን አዲስ ለሚገነቡ መኖሪያ ቤቶችም የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል። በመርሃ ግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ታድመዋል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












