፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 25 2016| NBC ETHIOPIA- የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ገልጻል።
የጋራ ግብረ ኃይሉ ሕዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች ከወዲሁ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር በመግባት ተልዕኮውን እየተወጣ እንደሚገኝ አመልክቷል፡፡
ሕዝቡም የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት የሚያውኩ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ከጋራ ግብረ-ኃይሉ ጎን በመሆን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ግብረ-ኃይሉ ጠይቋል፡፡
ግብረ-ኃይሉ ለመላው የዕምነቱ ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆን መመኘቱን ከፌደራል ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመልክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












