፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 23 2016| NBC ETHIOPIA-ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለዓባይ ግድብ ከአንድ ቢሊዮን 114 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ተነገረ፡፡
-በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና እድገትን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ውይይትና የጋራ መግባባትን መፍጠር ይገባል አለ የሰላም ሚኒስትር፡፡
-የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከ14ሺ በላይ በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን ማስመረጡን አስታወቀ፡፡
-ለ2016/17 የምርት ዘመን ከ12 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጂቡቲ ወደብ መድረሱ ተነገረ፡፡
-በ35 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የሚተገበርና ለአርብቶ አደሩ የጤና ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።
-ህብረተሰቡ መጪውን የትንሳኤን በዓል ሲያከብር ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ ተጋላጭ እንዳይሆን ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል አለ የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፡፡
-የዘንድሮው የሠራተኞች ቀን ‹‹ለሰላምና ለኑሮ ውድነት መፍትሄ እንሻለን›› በሚል መሪ ሃሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ135ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ49ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው፡፡
-በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራው የአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች በኢፌዴሪ አየር ኃይል ጉብኝት አድርገዋል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












