፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 21 2016| NBC ETHIOPIA-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በኮሪደር ልማት የፈረሰውን መሀሙድ ሙዚቃ ቤትን በአዲስ መልክ ለመገንባት የሁለገብ ህንጻ ግንባታን አስጀምሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን ጨምሮን ሊቀን ጳጳሳት ተገኝተዋል

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማዋን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ የመንገድ ኮሪደር ስራ እየተከናወነ መሆነን አንስተው በፒያሳ አከባቢ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የነበረው በተለምዶ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት የተሰኘው ህንጻ መፍረሱ ገልጸዋል።
በመልሶ ግንባታው ባለ 4 ወለል ህንጻ ውብ በሆነ መልኩ እንደሚሰራ ተናግረዋል።ግንባታውም በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ወራት እንደሚጠናቀቅ አንስተዋል።

በኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህንጻን ምትክ የሚሰራው ህንጻ በፒያሳ አራዳ ህንጻ ፊት ለፊት ይገኛል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












