Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በአለም አዲስ የተሰሙ አስገራሚ ጉዳዮች

April 18, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሚያዚያ10 2016| NBC ETHIOPIA-አለም በየቀኑ አስገራሚ አወዛጋቢ እና ለጆሮ አዲስ የሆኑ ክስተቶችን ከየአቅጣጫው ጀባ ሳትል ጀምበር ወታ አትጠልቅም።


በአጋጣሚም ሆነ ታስቦበት የሚደረጉት እነዚህ አስገራሚ ክስተቶች ሳቅን ከማጫር አልፈው አነጋጋሪነታቸው ዘላቂ ሲሆን ይስተዋላል።


እኛም ለዛሬ በአለም ዙሪያ ከተሰሙ አስገራሚ ክስቶች እና ውሳኔዎች የተመረጡትን ልንነግራቹ ውደድን                 


ብዙዎቻችን ስርቆት ሲባል ወደ አእምሮችን ቀድሞ የሚመጣው ከቁስ ስርቆት የዘለለ አይደለም ነገር ግን ከሰሞኑ የተሰማው ስርቆት አለምን አጃኢብ ያሰኘ ክስተት መሆን ችሏል።

Matthew David ኬይራንስ የተሰኘ ግለሰብ ለ35 አመታት የሌላ ሰው ማንነት  በመስረቅ ሲጠቀምበት ቆይቶ መያዙ  ነው የተገለጸው።

የአዮዋ ዩኒቨርሲቲ  ሆስፒታል ሰራተኛ የሆነው ግለሰቡ እ.ኤ.አ በ1988 በአልቡከርኪ ኒው ሜክሲኮ በሚገኝ የ ሆት ዶግ መሸጫ አብሮት ይሰራ ከነበረው ዶናልድ ዉድስ የተባለ ሰው ማንነት ወስዶ ለ35 አመት ሲጠቀምበት ቆይቷል።

ለፍርድ ቤት የቀረቡት  ሰነዶች ግለሰቡ  እ.ኤ.አ. በ1990 የተጭበረበረ የኮሎራዶ መታወቂያ ካርድ በዶናልድ ዉድስ  ስም እና የልደት ቀን ማውጣቱን እና በ1991ም በዉድስ ስም በሁለት ቼኮች መኪና መግዛቱን እንድሚያሳዩ ተገልጾል ።

Matthew David ኬይራንስ የልጆቹን ስም ሳይቀር በሰረቀው ማንነት እዲጠሩም አድሮ ቆይቷል። ነገር ግን በ2012 የስርቆቱን ደረጃ ከፍ አድርጎ ስለ ዉድስ ቤተሰብ  Ancestry.com ከተባለ በይነ መረብ ላይ ያገኘውን መረጃ በመጠቀም ከኬንታኪ ግዛት የዶናልድ ዉድስን የልደት ሰርተፍኬት በህገ-ወጥ መንገድ በማስወጣት አሁን ይሰራበት ወደነበረው ሆስፒታል እንደተዛወረ ተነግሮል።

ከ2016 እስከ 2022  ባጠቃላይ 200ሺ የአሜሪካን ዶላር  የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን እና ብድሮችን  በሰረቀው ማንነት ስም ወስዷል። 

በዚህ መሀል ትክክለኛው ዊሊያም ዶናልድ ዉድስ በሎሳን ጀለስ ከተማ ጎዳና ተዳዳሪ ሆኖ ተገኘቷል ።

የሱን ክሬዲት ካርድ በመጠቀም ከፍተኛ ብድር እየተወስደበት እንደሆነ የተገነዘበው ትክክለኛው ዉድስ ለባንክ ቢያመልክትም  ማንነቱን የሰረቀው ግለሰብ የራሱን  ስልክ በማስገባቱ  እና ለሚጠይቀው ጥያቄወች ትክክለኛ ምላሽ በመስጠቱ ባንኩ ለፖሊሲ በማመልከት ሁለቱ እንዲገናኙ ያደርጋቸዋል።

በጊዜውም David ኬይራንስ  ሐሰተኛው የዉድስን ሶሻል ሴኩሪቲ ካርድ እና የልደት የምስክር ወረቀት እንዲሁም መንጃ ፍቃድ ቅጂ በመላክ እውነተኛ እንደሆነ ማሳመን ችሎም ነበር።

በዚም እውነተኛው ዊልያም ዉድስ በወቅቱ ጎዳና ተዳዳሪ በመሆኑ ሰሚ ሳያገኝ ፖሊስ በማንነት ስርቆት እና በሃሰት አስመስሎ በመቅረብ  አስሮት እንደነበር ኦዲቲ ሴንተራል በገጹ አስነብቧል።

ነገር ግን በተደጋጋሚ እሱ ትክክለኛው ዉድስ መሆኑን አጥብቆ በመናገሩ እ.ኤ.አ. በ 2020  ለፍርድ ለመቅረብ የአእምሮ ብቃት እንደሌለው በመግለጽ በካሊፎርኒያ ወደሚገኝ የአእምሮ ሆስፒታል እንዲላክ ተድርጎ ህክምና ሲደርግለት እንድቆየ ተገልጾል ።

ከወጣም ቡኃላ ሁለት አመት በአእምሮ ሆስፒታል ውስጥ ያሳለፈውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ በሁለት አመት እስራት እና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ እና ዊሊያም ዉድስ የሚለውን ስም መጠቀም እንዲያቆም ተነግሮት ከእስር እንዲወጣ ተድርጎ ነበር።

ዉድስ ግን ሌላ ሰው ማንነቱን እየተጠቀመበት እንደሆነ እርግጠኛ ስለነበር ፍርድ ቤቱ እንዳዘዘው አሜን ብሎ አልተቀመጠም ይልቁንም ማንነቱን የሰረቀው ሰው ይኖሩበት የነበረውን የሃርትላንድ ፖሊስ መምሪያን ጨምሮ ከብዙ የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች ጋር በመገናኘት እንደ አዲስ ምርመራ እንዲጀመር አስደረገ።

ግራ የተጋባው ፖሊስም የሁለቱንም የልደት ምስክር ወረቀት ከተመለከተ በኋላ ሁለቱም ከዉድስ አባት ላይ በተወሰደ ናሙና የዘረመል ምርመራ በማድረግ ማነኛቸው እየዋሹ እንድሆነ መለየት ችሏል።

ከዚም በኋላ ሲያጭበረብር የቆየው ኪየርንስ  “ህይወቴ አብቅቷል “ሁሉም ነገር አልፏል” በማለት ለ35 አመታት የሌላ ሰውን ማንነት እንዴት እንደተጠቀመ መናዘዙ ተዘግቧል።

እስካሁን የፍርድ ሂደቱ ባያልቅም በሰራቸው ወንጀሎች እስክ 30 አመት እስራት ሊጠብቀው እንደሚችል ኦዲቲ ሴንተራል አስነብቧል።

ሌላኛው አስገራሚ ጉዳያችን በዘፈን ላይ አዲስ እገዳ መጣሉዋ ወደ ተሰማበት የራሽያ ግዛት ቼቼኒያ ያመራናል።

ቼቼኒያ በጣም ፈጣንም ወይም በጣም ቀርፋፋ  ተብለው  የሚታሰቡ  የሩሲያ  ሙዚቃን አግጃለው ብላለች።  

ውሳኔውም የተላለፈው በምዕራባውያን ወግ አጥባቂ እሴቶች የሚመጣ መበከልን ለመከላከል እንደሆነ ተገልጾል።

ከቼቼ ወይም ከቺቺኒያ ማህበረሰብ  አስተሳሰብ እና የሪትም ስሜት ጋር የሚጣጣም የሙዚቃ፣ የድምጽ እና የኪሪዮግራፊያ ስራዎች በደቂቃ ከ80-116 ቤቶች ብቻ የሚመቱ መሆን እንዳለባቸው ተደንግጓል። 

በዚም ሳቢያ የቼቼን አርቲስቶች ከአዲሶቹ መስፈርቶች ጋር የማይጣጣሙ ሙዚቃዎችን እስከ ሰኔ 1 ድረስ እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል አንዳለባቸው የሩሲያን ሚዲያ  ዋቢ አድርጎ ኦዲቲ ሴንተራል ዘግቦል።

እገዳውም ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ ብዙ የምዕራባውያን ዘፈኖችን ፣  ፖፕ፣ ዲስኮ እና ሮክን ጨምሮ በርካታ ዘውጎች  እንደሚከለክል ይጠበቃል።  ይህም የቼቼንስ ማህበረሰብ  በራሳቸው ባህላዊ የሙዚቃ ዘውጎች እንዲደሰቱ ያደርጋቸዋል ነው የተባለው።

በ-የአብስራ ብርሃኑ

ShareTweetShare
Previous Post

አጫጭር የስፖርት መረጃዎች

Next Post

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
አጫጭር የውጭ መረጃዎች

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት 75 በመቶ መድረሱ ተገለጸ

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት 75 በመቶ መድረሱ ተገለጸ

ያልተጠበቀ እድገት ያስመዘገበው የቻይና ኢኮኖሚ

ያልተጠበቀ እድገት ያስመዘገበው የቻይና ኢኮኖሚ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?