፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ10 2016| NBC ETHIOPIA-አለም በየቀኑ አስገራሚ አወዛጋቢ እና ለጆሮ አዲስ የሆኑ ክስተቶችን ከየአቅጣጫው ጀባ ሳትል ጀምበር ወታ አትጠልቅም።
በአጋጣሚም ሆነ ታስቦበት የሚደረጉት እነዚህ አስገራሚ ክስተቶች ሳቅን ከማጫር አልፈው አነጋጋሪነታቸው ዘላቂ ሲሆን ይስተዋላል።
እኛም ለዛሬ በአለም ዙሪያ ከተሰሙ አስገራሚ ክስቶች እና ውሳኔዎች የተመረጡትን ልንነግራቹ ውደድን
ብዙዎቻችን ስርቆት ሲባል ወደ አእምሮችን ቀድሞ የሚመጣው ከቁስ ስርቆት የዘለለ አይደለም ነገር ግን ከሰሞኑ የተሰማው ስርቆት አለምን አጃኢብ ያሰኘ ክስተት መሆን ችሏል።
Matthew David ኬይራንስ የተሰኘ ግለሰብ ለ35 አመታት የሌላ ሰው ማንነት በመስረቅ ሲጠቀምበት ቆይቶ መያዙ ነው የተገለጸው።
የአዮዋ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ሰራተኛ የሆነው ግለሰቡ እ.ኤ.አ በ1988 በአልቡከርኪ ኒው ሜክሲኮ በሚገኝ የ ሆት ዶግ መሸጫ አብሮት ይሰራ ከነበረው ዶናልድ ዉድስ የተባለ ሰው ማንነት ወስዶ ለ35 አመት ሲጠቀምበት ቆይቷል።
ለፍርድ ቤት የቀረቡት ሰነዶች ግለሰቡ እ.ኤ.አ. በ1990 የተጭበረበረ የኮሎራዶ መታወቂያ ካርድ በዶናልድ ዉድስ ስም እና የልደት ቀን ማውጣቱን እና በ1991ም በዉድስ ስም በሁለት ቼኮች መኪና መግዛቱን እንድሚያሳዩ ተገልጾል ።

Matthew David ኬይራንስ የልጆቹን ስም ሳይቀር በሰረቀው ማንነት እዲጠሩም አድሮ ቆይቷል። ነገር ግን በ2012 የስርቆቱን ደረጃ ከፍ አድርጎ ስለ ዉድስ ቤተሰብ Ancestry.com ከተባለ በይነ መረብ ላይ ያገኘውን መረጃ በመጠቀም ከኬንታኪ ግዛት የዶናልድ ዉድስን የልደት ሰርተፍኬት በህገ-ወጥ መንገድ በማስወጣት አሁን ይሰራበት ወደነበረው ሆስፒታል እንደተዛወረ ተነግሮል።
ከ2016 እስከ 2022 ባጠቃላይ 200ሺ የአሜሪካን ዶላር የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን እና ብድሮችን በሰረቀው ማንነት ስም ወስዷል።
በዚህ መሀል ትክክለኛው ዊሊያም ዶናልድ ዉድስ በሎሳን ጀለስ ከተማ ጎዳና ተዳዳሪ ሆኖ ተገኘቷል ።
የሱን ክሬዲት ካርድ በመጠቀም ከፍተኛ ብድር እየተወስደበት እንደሆነ የተገነዘበው ትክክለኛው ዉድስ ለባንክ ቢያመልክትም ማንነቱን የሰረቀው ግለሰብ የራሱን ስልክ በማስገባቱ እና ለሚጠይቀው ጥያቄወች ትክክለኛ ምላሽ በመስጠቱ ባንኩ ለፖሊሲ በማመልከት ሁለቱ እንዲገናኙ ያደርጋቸዋል።
በጊዜውም David ኬይራንስ ሐሰተኛው የዉድስን ሶሻል ሴኩሪቲ ካርድ እና የልደት የምስክር ወረቀት እንዲሁም መንጃ ፍቃድ ቅጂ በመላክ እውነተኛ እንደሆነ ማሳመን ችሎም ነበር።
በዚም እውነተኛው ዊልያም ዉድስ በወቅቱ ጎዳና ተዳዳሪ በመሆኑ ሰሚ ሳያገኝ ፖሊስ በማንነት ስርቆት እና በሃሰት አስመስሎ በመቅረብ አስሮት እንደነበር ኦዲቲ ሴንተራል በገጹ አስነብቧል።
ነገር ግን በተደጋጋሚ እሱ ትክክለኛው ዉድስ መሆኑን አጥብቆ በመናገሩ እ.ኤ.አ. በ 2020 ለፍርድ ለመቅረብ የአእምሮ ብቃት እንደሌለው በመግለጽ በካሊፎርኒያ ወደሚገኝ የአእምሮ ሆስፒታል እንዲላክ ተድርጎ ህክምና ሲደርግለት እንድቆየ ተገልጾል ።
ከወጣም ቡኃላ ሁለት አመት በአእምሮ ሆስፒታል ውስጥ ያሳለፈውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ በሁለት አመት እስራት እና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ እና ዊሊያም ዉድስ የሚለውን ስም መጠቀም እንዲያቆም ተነግሮት ከእስር እንዲወጣ ተድርጎ ነበር።
ዉድስ ግን ሌላ ሰው ማንነቱን እየተጠቀመበት እንደሆነ እርግጠኛ ስለነበር ፍርድ ቤቱ እንዳዘዘው አሜን ብሎ አልተቀመጠም ይልቁንም ማንነቱን የሰረቀው ሰው ይኖሩበት የነበረውን የሃርትላንድ ፖሊስ መምሪያን ጨምሮ ከብዙ የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች ጋር በመገናኘት እንደ አዲስ ምርመራ እንዲጀመር አስደረገ።
ግራ የተጋባው ፖሊስም የሁለቱንም የልደት ምስክር ወረቀት ከተመለከተ በኋላ ሁለቱም ከዉድስ አባት ላይ በተወሰደ ናሙና የዘረመል ምርመራ በማድረግ ማነኛቸው እየዋሹ እንድሆነ መለየት ችሏል።
ከዚም በኋላ ሲያጭበረብር የቆየው ኪየርንስ “ህይወቴ አብቅቷል “ሁሉም ነገር አልፏል” በማለት ለ35 አመታት የሌላ ሰውን ማንነት እንዴት እንደተጠቀመ መናዘዙ ተዘግቧል።
እስካሁን የፍርድ ሂደቱ ባያልቅም በሰራቸው ወንጀሎች እስክ 30 አመት እስራት ሊጠብቀው እንደሚችል ኦዲቲ ሴንተራል አስነብቧል።
ሌላኛው አስገራሚ ጉዳያችን በዘፈን ላይ አዲስ እገዳ መጣሉዋ ወደ ተሰማበት የራሽያ ግዛት ቼቼኒያ ያመራናል።

ቼቼኒያ በጣም ፈጣንም ወይም በጣም ቀርፋፋ ተብለው የሚታሰቡ የሩሲያ ሙዚቃን አግጃለው ብላለች።
ውሳኔውም የተላለፈው በምዕራባውያን ወግ አጥባቂ እሴቶች የሚመጣ መበከልን ለመከላከል እንደሆነ ተገልጾል።
ከቼቼ ወይም ከቺቺኒያ ማህበረሰብ አስተሳሰብ እና የሪትም ስሜት ጋር የሚጣጣም የሙዚቃ፣ የድምጽ እና የኪሪዮግራፊያ ስራዎች በደቂቃ ከ80-116 ቤቶች ብቻ የሚመቱ መሆን እንዳለባቸው ተደንግጓል።
በዚም ሳቢያ የቼቼን አርቲስቶች ከአዲሶቹ መስፈርቶች ጋር የማይጣጣሙ ሙዚቃዎችን እስከ ሰኔ 1 ድረስ እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል አንዳለባቸው የሩሲያን ሚዲያ ዋቢ አድርጎ ኦዲቲ ሴንተራል ዘግቦል።
እገዳውም ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ ብዙ የምዕራባውያን ዘፈኖችን ፣ ፖፕ፣ ዲስኮ እና ሮክን ጨምሮ በርካታ ዘውጎች እንደሚከለክል ይጠበቃል። ይህም የቼቼንስ ማህበረሰብ በራሳቸው ባህላዊ የሙዚቃ ዘውጎች እንዲደሰቱ ያደርጋቸዋል ነው የተባለው።
በ-የአብስራ ብርሃኑ












