፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 10 2016| NBC ETHIOPIA- የ90 ዓመት እድሜ እንዳለው የሚነገርለት የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እድሳት መገባደዱን የካቴድራሉ አስተዳደርና ሰበካ ጉባኤ አስታውቋል።
ካቴድራሉ ታሪካዊነቱን ጠብቆ እንዲታደሰ በቅዱስ ሲኖዶስ ፍቃድ በካቴድራሉ አስተባባሪነት እና በቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን እገዛ ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት ተጀምሯል።

እድሳቱ በውሉ መሰረት መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም መጠናቀቅ ቢጋባውም በገቢ ማነስ እና ህንፃውን ለማጠናቀቅ የሚረዱ ግብአቶች ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር መሆኑ ተገልጿል።

የቀረውን ስራ ለማጠናቀቅ 85 ሚሊዮን ብር እንደሚፈልግ ተነግሯል። እስከ ፍፃሜው ለማድረስ ሁሉም ምዕመን እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












