Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

የእብድ ውሻ በሽታ (RABIES)

April 17, 2024
in Health
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ 

አዲስ አበባ | ሚያዚያ 09 2016| NBC ETHIOPIA- የእብድ ውሻ በሽታ በእንግሊዘኛው አጠራር ሬቢስ ከሒንዱ ሳንስክሪት ራብሐስ (Rabhas) ቃል የፈለሰ ሲሆን ይህ በሽታ ዝምተኛ፣ ለጌታው ታዛዥና ጓደኛ የነበረ ውሻ በድንገት ወደ አስፈሪ የአውሬነት ባህሪ የሚለወጥበት ሁኔታ ያሳያል። የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) በቫይረስ አማካኝነት በበሽታው ከተለከፈ እንስሳ ወደ ሌላ ጤነኛ እንስሳ ወይም ወደ ሰው በንክሻ የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ውሻን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ደመ ሞቃትና አጥቢ የሆኑ እንስሳትን እንዲሁም ሰውን የሚያጠቃ በሽታ ነው።

ውሻን የሚያሳብደው በሽታ ራብዶቫይረስ በተባለ ቫይረስ የሚመጣ በሽታ ሲሆን፤ ሁሉንም ደመ ሞቃት አጥቢ እንስሳትን ፣ ሰውንም ጨምሮ የሚያጠቃ ነው። ቫይረሱ ወደ ተነካሹ አካል ከገባ በኃላ ለመራባት የግድ ራሱን ከነርቭ ሕዋስ ጋር ማጣበቅ ይኖርበታል። የዚህን በሽታ ቫይረስ ከሌሎች የቫይረስ አይነቶች ልዩ የሚያደርገው መኖሪያው ወይም መራቢያው በነርቭ ሕዋስ በአመዛኙ አንጎል ውስጥ መሆኑ ነው።

የበሽታው ዋና መተላለፊያ መንገድ ንክሻ ነው፤ ነገር ግን በበሽታው ከተለከፈ እንስሳ ጋር በሚደረግ ጥንቃቄ የጎደለው ንክኪ በተለይ የአበደው እንስሳ ለሀጭ ባልተሸፈነ ቁስል ላይ ሲያርፍ የበሽታው ቫይረስ ወደ ጤነኛ ሰውም ሆነ እንስሳ አካል ገብቶ በሽታው ሊተላለፍ ይችላል። በአለም እስካሁን ድረስ በምርምር በሽታው ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ የተረጋገጠ መረጃ የለም።

ውሻን የሚያሳብድ በሽታ በተለምዶ ስሙ የእብድ ውሻ በሽታ እየተባለ ይጠራ እንጂ በበሽታው የሚጠቁ እንስሳት ብዙ ናቸው፡፡ ውሻን በሚያሳብድ በሽታ ከሚጠቁ የቤት እንስሳት ውስጥ ድመት፣ በሬ፣ ላም፣ በግ፣ ፍየል፣ አህያ፣ ፈረስና በቅሎ እንዲሁም ከዱር እንስሳት ቀበሮና የለሊት ወፍ ተጠቃሽ ናቸው።

የበሽታው ምልክቶች በሰውም ሆነ በእንስሳት ላይ የሚታዩት የቫይረሱ የመራቢያ ወይም የመደራጃ ጊዜውን በአንጎል ክፍል ከጨረሰ በኋላ ነው። ቅድመ ሕመም (Incubation Period) የምንለው አንድ ሰው ከተነከሰበት ቀን ጀምሮ የሕመም ምልክት እስከሚጀመረበት ያለውን የቫይረሱን የመደራጃ ጊዜ ነው። የቫይረሱን የመራቢያ ጊዜ አጭር ወይንም ረጅም መሆኑን የሚወስኑት የቁስሉ ጥልቀት ወይም ስፋት፣ በንክሻው ጊዜ የገባው የቫይረስ መጠን፤ የሰውየው በሽታ የመከላከል አቅም ናቸው። ቁስሉ እየሰፋና እየተለቀ በሄደ ቁጥር የሚገባው የቫይረስ መጠን እጅግ የበዛ ሲሆን ወይም ቫይረሱ የነርቭ ሕዋስን የማግኘት እድሉ እየጨመረ ስለሚሄድ የመራቢያ ጊዜው አጭር ይሆናል።

በበሽታው የተጠቃ ሰው በመጀመሪያ ንክሻው የደረሰበት አካባቢ መለብለብ፣ መደንዘዝ፣ መዛል ያጋጥመዋል። እየቆየም ሲሄድ ሄድ መለስ የሚል የመዋጥ መቸገር፣ ለሃጭ መዝረክረክ፣ ራስን ችሎ መቆም አለመቻል፣ የማስታወስ ችግር፣ መቃዠት፣ ትኩሳት፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ይኖረዋል፡፡ ወደ 10ኛው ቀን ላይ ደግሞ ራሱን ሙሉ ለሙሉ ይስትና ኮማ ውስጥ ይገባል።

የእብድ ውሻ በሽታ ህክምና

???? አንዳንድ ጊዜ ንክሻ የፈጸመው እንስሳ ወይም ውሻ ክትባት የተከተበ ከሆነና ወደ ምርመራ ተቋም መውሰድ ካልተቻለ እንስሳው ባለበት አስሮ ለ10 ቀናት መከታተል የሚቻል ሲሆን እንስሳው በተጠቀሰው ቀነ ገደብ ውስጥ ሰንሰለቱን በጥሶ ቢጠፋ እንስሳው ውሻን በሚያሳብደው በሽታ ተለክፎ ሊሆን ይችላል የሚለውን ግምት በከፍተኛ ደረጃ ስለሚያጠናክረው ተነካሹ ግለሰብ ሁኔታውን ለጤና ባለሞያ ማሳወቅ ይኖርበታል።

????በዚህ አስር የክትትል ቀናት ውስጥ ምንም አይነት አካላዊም ሆነ ባህሪያዊ ለውጥ ካላሰየና ምግብ እየበላ፣ እየጠጣ በሕይወት ከቆየ ንክሻ በፈጸመበት ሰዓት ወደ ተነካሹ ሰው በሽታ አለማስተላለፉንና ተነካሹ ከበሽታው ነጻ መሆኑ ይረጋግጣል፡፡

????እንስሳው ከሞተ ደግሞ ጭንቅላቱን ቆርጦ ለምርመራ ወደ ህክምና ተቋም መላክ ያስፈልጋል፡፡ በእንስሳትም ሆነ በሰዎች በበሽታው ለመያዛቸው ለማረጋገጥ የሚያስችል የቅድመ ምርመራ የለም።

????ውሻን የሚያሳብድ በሽታ ምልክት ለታየበት ሰው ከበሽታው ለመፈወስ የሚደረግ የሕክምና እርዳታ ስለሌለ ሰዎች የመዳን እድላቸው በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ሰው ለበሽታው ሊያጋልጥ የሚችል ንክሻ ወይንም ከእንስሳው ምራቅ ወይም ለሀጭ ጋር ንክኪ ካለው ጊዜ ሳይሰጡ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል።

የመጀመሪያ የሕክምና ዕርዳት

????የተነከሰው አካል በውሃና በሳሙና ወይም በአልኮል በደንብ ማጠብ፤ ይህም ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም በመጠኑ ቫይረስ መጠን ይቀንሳል።

????ንክሻ የፈጸመው እንስሳ በሕይወት ካለ ለእንስሳት ሐኪም አሳይቶ ለ10 ቀን ክትትል እንዲደረግለት መደረግ አለበት።

????በልዩ ልዩ ምክንያት በክትትል ላይ ያለው እንስሳ ቢያመልጥ ተነካሹ ሰው ወዲያውኑ የመከላከያ ክትባት መውሰድ ይኖርበታል።

????ንክሻ የፈጸመው እንስሳ በበሽታው ተለክፏል ተብሎ የሚጠረጠር ከሆነ እንስሳውን ገድሎ ወይንም በ10 ቀን ክትትል ጊዜ ውስጥ ቢሞት ጭንቅላቱን ቆርጦ እንዲመረመር ማድረግ አለበት፡፡ የቀረውን የሰውነት ክፍል (በድን) ማቃጠል ወይም አርቆ መቅበር ያስፈልጋል። ይህም ከሚመለከታቸው የህብረተሰብና የእንስሳት ጤና ባለሞያዎች ጋር ቢደረግ ተመራጭ ነው።

????የእንስሳው ጭንቅላት ተመርምሮ በበሽታው ተጠቂ መሆኑ ከተረጋገጠ ተነካሹ ሰው በአስቸኳይ የመከላከያ ክትባት መከታተል ይኖርበታል።

????በበሽታው ተይዞ ሕመሙ የጀመረው ሰው ለሀጭ ማዝረብረብና ለመናከስም ስለሚከጅል በጥንቃቄ ማስታመም አስፈላጊ ነው፡፡ ከለሀጭ ጋር ከሚደረግ ንክኪ ባሻገር በሽተኛው አስታማሚው ፊት ላይ ሊተፋ ስለሚችል በሽተኛውን በጣም ባይቀርቡት ይመረጣል፡፡

????የእጅ መሸፈኛ ላስቲክ ወይም ጓንት በማድረግ ማስታመምና የሚፈለገውን እርዳታ መስጠት ይቻላል፡፡ ለበሽተኛው የሚፈለገው እርዳታ ከተከናወነ በኋላ በደንብ እጅና ፊትን በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ለሚደረግ ማንኛውም ለበሽታው የሚያጋልጥ ንክኪ ሲኖር ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።

የመከላከያ ክትባት

????የንክሻው ዓይነት ከበድ ያለ ከሆነ በተለይም ከአንገት በላይ የተፈጸመ ንክሻ ከሆነ እንዲሁም ንክሻው ሰፋ ያለ ቦታ የሚሸፍን ከሆነ የእንስሳው የ10 ቀን ክትትል ውጤት እስኪታወቅ ድረስ ተነካሹ የመከላከያ ክትባት መጀመር ይኖርበታል።

????በተጨማሪም ኢሙኖግሎቡሊን (Rabies Immunoglobulin) በቁስሉ ዙርያ በመስጠት ቫይረሱ ወደ ነርቭ እንዳይሰራጭ እዚያው በተወሰነ ደረጃ ለማገድ ይረዳል፡፡

????ውሻን ለሚያሳብደው በሽታ መከላከያ ክትባት ለሰዎች የሚሰጠው በሁለት አይነት ሁኔታዎች ነው፡፡ እነዚህም ቅድመ-ንክሻ እና ድህረ-ንክሻ መከላከያ ክትባት በመባል ይታወቃሉ፡፡

????ቅድመ-መጋለጥ ክትባት (Pre-exposure) የሚባለው ከእንስሳት ጋር በቅርበት ለሚሰሩ ባለሞያዎች፤ ለእንስሳት ሀኪሞች፤ የበሽታው ምርመራ በሚከናወንበት ላብራቶሪ ውስጥ ለሚሰሩ፤ በዱር እንስሳት ጥበቃና ፓርክ ሰራተኞች፤ በሆስፒታል የጤና ባለሞያዎችና ተጓዦች በተለየ መልኩ ለበሽታው ሊጋለጡ ስለሚችሉ የሚሰጥ የመከላከያ ክትባት አይነት ነው፡፡

????ድህረ-መጋለጥ መከላከያ ክትባት (Post-exposure) የሚባለው ደግሞ በተለይ የበሽታው አምጪ የሆነው ቫይረስ በንክሻም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ የሚሰጥ ክትባት ነው፡፡ ይህም የመከላከያ ክትባት መውሰድ የሚገባቸው በበሽታው ተለክፏል ተብሎ በተጠረጠረ ወይም በተረጋገጠ እብድ እንስሳ የተነከሱ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡

Tags: healthrabiesrabies vaccine
ShareTweetShare
Previous Post

የዘለንስኪ ጥሪ

Next Post

የሀረሪ ሙዚቃ ላይ ጥልቅ ጥናት የተደረገበት መፅሀፍ ተመረቀ

Related Posts

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ
Health

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ

June 15, 2026
38
በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው
Health

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው

June 4, 2026
24
⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ
Health

⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ

March 16, 2026
85
“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ
Health

“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ

February 17, 2026
48
ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ
Health

ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ

January 21, 2026
42
ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና
Health

ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና

August 25, 2025
89
Next Post
የሀረሪ ሙዚቃ ላይ ጥልቅ ጥናት የተደረገበት መፅሀፍ ተመረቀ

የሀረሪ ሙዚቃ ላይ ጥልቅ ጥናት የተደረገበት መፅሀፍ ተመረቀ

በሃገረ ጀርመን እና በእንግሊዝ የተከሰቱ አስገራሚ እውነታዎች

በሃገረ ጀርመን እና በእንግሊዝ የተከሰቱ አስገራሚ እውነታዎች

የሀገር ውስጥ አጫጭር መረጃዎች

የሀገር ውስጥ አጫጭር መረጃዎች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?