፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሚያዚያ 09 2016| NBC ETHIOPIA- “ክውን ጥበብ፥ ከመገኛ ምንጩ” የተሰኘ እና በአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ በተዘጋጀ የጥናት ቡድን የተጠና የጥናት ውጤት መፅሀፍ በሐረር ከተማ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
መፅሀፉ በሐረሪ ማህበረሰብ ቱባ የዜማ ባህል እና የሙዚቃ ቅኝቶች ዙሪያ ያጠነጠነ ነው።አምስት ምዕራፎች ያሉት መፅሀፉ፥ በሀረሪ የሙዚቃ ስልት ላይ ግንዛቤ ለመስጠት፣ እውቀት እንዲሰፋ ለማድረግ አስተዋፅዖ የጎላ እንደሚኖረው በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ተገልጿል።
የሐረሪን ሙዚቃ ከቀሪው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋር ለማስተዋወቅ እንዲሁም የባህል መደበላለቀቅ ለማጥራት ጥናቱ ያግዛልም ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ጥናቱ ወጥ የሆነ የሐረሪ ሙዚቃ ምት እና ሥልት ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ለሌሎች ጥናቶች እንደመነሻ ሊሆን እንደሚችልም ተነስቷል።
በምረቃ ስነስርዓቱ የሀረሪ ክልል ዋና አፈጉባኤ ሙሀዲን አህመድ ፣የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ሰረጸ ፍሬስብሀትን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በ-ሰላማዊት ወንድወሰን
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












