Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የዋጋ ቅናሽ ያሳየው ነዳጅ

April 16, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሚያዚያ 08 2016| NBC ETHIOPIA-እስራኤል ከሁለት ሳምንታት በፊት በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ፅህፈት ቤት ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ይታወሳል፡፡ ኢራን በደማስቆ ለደረሰው ጥቃት የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት ወደ እስራኤል ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች፡፡ ይህንንም ተከትሎ በእስያ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ዋጋ መቀነሱ ተሰምቷል፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ተመንን የሚዘውረው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል 90 ዶላር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ ላለፉት ስድስት ወራት የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ አሻቅቦ የነበረ ሲሆን ኢራን በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ ዋጋው በ 1በመቶ ሊቀንስ ችሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሚል 92.18 ዶላር የነበረ ሲሆን ከጥቅምት ወር ወዲህ ዋጋው ከፍተኛ ነበር፡፡ ተንታኞች እስራኤል ለጥቃቱ ምላሽ የምትሰጥ ከሆነ በአለም ገበያ ወሳኝ የንግድ ለውጦችን ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ቅድመ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ሀገሪቷ በእስራኤል ላይ ያደረሰችው ጥቃት ተፅእኖው በዓለም ዓቀፍ የነዳጅ ዋጋ ብቻ ሳይሆን በእስያ-ፓሲፊክ ቀጠና የአክሲዮኖች ሽያጭ ዋጋ ገና ከአሁኑ ማሽልቆል ጀምሯል፡፡ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ሃንግ ሴንግ፣ የጃፓኑ Nikkei 225 እና በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ኮስፒ ሲያካሄዱት የነበረው የአክሲዮን ሽያጭ መጠን መቀነሱን ቢቢሲ በቢዝነድ አምዱ አትቷል፡፡

ሌላኛው የዋጋ ጭማሪ ያሳየው ወርቅ ነው፡፡ 31.1 ግራም የሚመዝነው አንድ አውንስ ወደ 2,400 ዶላር የሚጠጋ ዋጋ ጨምሯል፡፡ የወርቅ ንግድ አስተማማኝ ኢንቬስትመንት አይነቶች ከሚባሉት መሃከል ሲሆን በሚያስደንቅ ሁኔታ የዋጋ ለውጥ ሊያሳይ ችሏል፡፡ በኦማን እና በኢራን መካከል ያለው የባህር ዳርቻ በሆርሙዝ ሰርጥ  ዋነኛው የባህር ትራንስፖርት የሚካሄድበት መንገድ ሲሆን ከዓለም አጠቃላይ የነዳጅ አቅርቦት 20% ያህሉ የሚጓዝበት መስመር ነው፡፡

 የዘርፉ ባለሙያዎች በፐርሺያ  እና በኦማን ባሕረ ሰላጤ መካከል በሚገኘው የሆርሙዝ የባህር ዳርቻን፤ በአማራጭነት መጠቀም በንግድ መስመሩ እንዲሁም በቀጣይነት የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ተፅዕኖ እንዳይፈጥር ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ የኦፔክ አባል ሀገራት ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ኩዌት እና ኢራቅ የሆርሙዝ የባህር ዳርቻን በመጠቀም ነዳጅ ወደ ሌሎች ሀገራት ይልካሉ፡፡ 


ኢራን ከዓለም ሰባተኛዋ እንዲሁም ከኦፔክ አባል ሀገራት 3ተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ አምራች ሀገር መሆኗ ይታወቃል፡፡ በ2023 የኢራን ስታቲስቲክ ማእከል መረጃ እንደሚያሳየው ለሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት በ2023 የ7.9 በመቶ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን በተያዘው ዓመት የኢራን የነዳጅ ገቢዋም በ9 ወራት ውስጥ 34 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር፡፡ ሀገሪቷ በቀን ከ3 ሚሊዮን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅን ታመርታለች።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች "ክስተቱ የተወሳሰበ እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ እና በሰብአዊ ቀውሶች ላይ የሚፈጥረው አንድምታ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ በመካከለኛው ምስራቅ በስፋት የተስፋፋው ግጭት የኃይል ዋጋ እንዲጨምር  እና የማዕከላዊ ባንኮች የዋጋ ንረትን ለማውረድ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሊገቱ ይችላሉ በሚል ስጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2022 ሩሲያ ዩክሬንን በወረረችበት ወቅት ምዕራባውያን ሀገራት ከዓለም ዋና ዘይት ላኪዎች አንዷ በሆነችው ሩሲያ ላይ ማዕቀብ በመጣላቸው የተነሳ የነዳጅ ዋጋ በበርሚል ወደ 120 ዶላር ጭማሪ ማሳየቱ ይታወሳል፡፡ 
የነዳጅ እና የኢነርጂ ዋጋ ላለፉት ሁለት ዓመታት ጭማሪ ማሳየቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚታየው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ዋነኛ መንስኤ ነው።ተንታኞች እስራኤል ለጥቃቱ የምትሰጠው ምላሽ በቀጣዮቹ ቀናት እና ሳምንታት የዓለም የገበያ ስርአት አሁን ካለበት ሁኔታ ሊቀይር የሚችል ይሆናል ብለዋል፡፡ 
Tags: crude oil price decreasecrude oliiran
ShareTweetShare
Previous Post

የሀገር ውስጥ አጫጭር መረጃዎች

Next Post

የዘለንስኪ ጥሪ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የዘለንስኪ ጥሪ

የዘለንስኪ ጥሪ

የእብድ ውሻ በሽታ (RABIES)

የእብድ ውሻ በሽታ (RABIES)

የሀረሪ ሙዚቃ ላይ ጥልቅ ጥናት የተደረገበት መፅሀፍ ተመረቀ

የሀረሪ ሙዚቃ ላይ ጥልቅ ጥናት የተደረገበት መፅሀፍ ተመረቀ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?