፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 27፣ 2016| NBC ETHIOPIA-ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 70 በመቶ የተሳታፊ ልየታ ስራው ከ70 በመቶ በላይ መድረሱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

በሰላም እጦት ሳቢያ በአማራ ክልል እንዲሁም በጦርነት የነበረው በትግራይ ክልል የተሳታፊ ልየታ አለመደረጉ ተነስቷል።
በክልሎች ተሳታፊ ልየታ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተካሄደ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሀገራዊ ምክክሩ ላይ ተሳታፊ ለመለየትና አጀንዳ ለማሰባሰብ አንፃራዊ ሰላም ያስፈልገናል ተብሏል።
ሙሉ በሙሉ የተሳታፊ ልየታ ያከናወኑ ክልሎችን አጀንዳ የማሰባሰብ መርሃግብር ከ15 ቀናት በኃላ ለማከናወን ማቀዱን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












