Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ቅዱስ ቁርአን ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጥራዝ የተሰበሰበበት አጋጣሚ

April 5, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | መጋቢት 27፣ 2016| NBC ETHIOPIA-ለሰው ልጆች መመሪያ ብሎም የህይወት ጎዳና ይሆን ዘንድ ከሰማይ ወደ ምድር የተወረዱ በርካታ ቅዱሳን መጽሀፍት ይገኛሉ፡፡

በእስልምና ሀይማኖት አስተምህሮ መሰረት ወደ ምድር ከወረዱ ሰማያዊ መጽሐፍት መካከል ዘቡር፣ ተውራት፣ ኢንጂል፣ ሱሁፍ እንዲሁም ቁርዓን ይጠቀሳሉ፡፡

ከነዚህም መካከል በነብዩ ሙሃመድ ላይ የወረደው ቁርዓን የመጨረሻው ሰማያዊ ቅዱስ መጽሀፍ ነው፡፡

ቁርዓን 114 ምዕራፎች፣604 ገጾች፣6ሺህ 3መቶ 48 አናቅጾች፣87ሺህ 5መቶ 30 ቃላት እንዲሁም 325ሺህ 3መቶ 84 ፊደላት አሉት፡፡

ቁርዓን በነብዩ ሙሃመድ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መውረድ የጀመረው ሂራ በተባለ ዋሻ ውስጥ ባለንበት የረመዳን ወር ነበር፡፡

ከዛም በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች በፈረንጆቹ ከ609 እስከ 632 ባሉት 23 አመታት ውስጥ ወርዶ ተጠናቋል፡፡

በቀደመው ጊዜ ቁርዓን ሲወርድ በቆዳ ላይ፣ በድንጋይ ላይ እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ይመዘገብ የነበረ ሲሆን በቃል መሸምደዱም አንዱ የመመዝገቢያ አማራጭ ነበር፡፡

ቁርዓን በዚህና መሰል መንገድ ሲመዘገብ ቆይቶ ከነብዩ ህልፈት በኋላ በአቡበክር የአስተዳደር ዘመን ይደርሳል፡፡

በሳቸው የአስተዳደር ዘመንም በተከሰተ አንድ ጦርነት ቁርዓንን በቃላቸው ሸምድደው የያዙ በርካታ የነብዩ ባልደረቦች በዚህ ጦርነት ህይወታቸው ያልፋል፡፡

ይህንን ያስተዋሉት የወቅቱ አስተዳዳሪ አቡበክር ሲዲቅ ቁርዓን እንዳይጠፋ በመስጋት በተለያዩ መንገዶች ተመዝግበው የተቀመጡ የቁርዓን አንቀጾች በአንድ እንዲሰበሰቡ ያደርጋሉ፡፡

ከዛም በመቀጠል የተሰበሰቡት የቁርዓን አንቀጾች ትክክለኛነት ለማረጋገጥም ቁርዓንን በቃላቸው የሸመደዱና በህይወት የሚገኙ ሰሃባዎች እንዲያረጋግጡት ካደረጉ በኋላ በአንድ ጥራዝ እንዲቀመጥ ማድረግ ቻሉ፡፡

ይሄኔ ነበር ቁርዓን ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጥራዝ አንድ ላይ ተሰብስቦ መቀመጥ የቻለው፡፡

ከአመታት በኋላም ሶስተኛው አስተዳዳሪ ኡስማን ቢን አፋን በአንድ ጥራዝ የተቀመጠውን ቁርዓን ወደ አራት በማብዛት አንዱን እሳቸው ጋር በማስቀመጥ የተቀሩትን በእስልምና አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሀገራት መሪዎች አንድ አንድ ቅጂ ላኩ፡፡

ከዚህ በኋላ ነበር ቁርዓን በከፍተኛ ፍጥነትና ቁጥር ታትሞ በአለም ዙሪያ ለሚገኙ ሙስሊሞች መድረስ የቻለው፡፡

አሁን ላይ ቅዱስ ቁርዓን በአለም ዙሪያ ከ800 ሚሊየን በላይ የቁርዓን ቅጂዎች እንደሚገኙ ይታመናል፡፡

በአለም ዙሪያ ሙሉውን ቁርዓን በቃላቸው ሸምድደው የያዙ ደግሞ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሀፊዞች እንደሚገኙ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ቁርዓንን አትመው የሚያሰራጩ ማተሚያ ቤቶች በአሁኑ ወቅት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሲሆን የሚያትሙበት መንገድ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው፡፡

የቁርዓን ህትመት የመጀመሪያ ተግባር ቃላቶቹን በእጅ ጽሁፍ ማስፈር ነው፡፡

በመቀጠል ደግሞ ይህ በእጅ የሰፈሩት የቁርዓን ቃላትን ወደ ዲጂታል እንዲቀየሩ ይደረጋል፡፡

ከዛም በመቀጠል ወረቀት የህትመቱ አካል መሆን ይጀምራል፡፡ወረቀቱ ከተለመዱት አሊያም ከምናውቃቸው የወረቀት አይነቶች የተለየ ነው፡፡ወረቀቱም ወደ ማተሚያው ማሽን እንዲሄድ ይደረጋል፡፡

ወደ ማተሚያ ማሽኑ የገባው ወረቀትም ያወጣውን የቁርዓን ፊደላትን በትክክል ያለ ምንም እንከን ያወጣ መሆኑ በቁርዓን አዋቂዎች ይገመገማል፡፡

900 ሺህ የቅዱስ ቁርኣን ገፆች ወደ ዋናው የክትትል ቡድን ሲሄዱ ከነዚህም መካከል የክትትል ቡድኑ ከታተሙት መካከል በማንሳት ናሙናዎች በመውሰድ ይገመግማል፡፡

በዚህም ግምገማ የተዘለለ አሊያም የተዛባ ቃልም ሆነ ፊደል ካለ እንዲወገድ ይደረጋል፡፡

በዚህ መልኩ የጥራት ደረጃውን ጠብቆ የታተመው ቁርዓን ወደ ተለያዩ ሀገራት ይሰራጫል፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

ሮዋን ሴባስቲያን አትኪንሰን ሚስተር ቢን

Next Post

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሳታፊ ልየታ ስራው ከ70 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሳታፊ ልየታ ስራው ከ70 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሳታፊ ልየታ ስራው ከ70 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ

ጃፓን በሩሲያ ዕቃዎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች

ጃፓን በሩሲያ ዕቃዎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?