፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 26፣ 2016| NBC ETHIOPIA- ደቡብ አፍሪካዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሉክ ፍለዎር በዘራፊዎች መገደሉ ተሰምቷል።
የ24 ዓመቱ የካይዘር ችፍስ ተከላካይ፣ ባሳለፍነው ሀሙስ በመኪና ጠላፊዎች በጥይት ተደብድቦ ህይወቱ ማለፉ ነው የተነገረው።
የህልፈቱ ዜና በጭምጭምታ ደረጃ ሲነገር የቆየ ሲሆን ክለቡ በትላንትናው ዕለት ማረጋገጫ ሰጥቷል።

ወጣቱ ተጨዋች በ2020 የቶክዮ ኦሊምፒክ አገሩን ወክሎ በ3ቱም ጨዋታዎች ላይ ቋሚ ተሰላፊ ነበር።
ሉክ ፍለዎር ከሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ወደ አንጋፋው ካይይዘር ችፍስ የተዘዋወረው በአምናው የውድድር ዓመት መጨረሻ ላይ እንደነበር መረጃው አክሏል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












