፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 26፣ 2016| NBC ETHIOPIA-ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ 500 ትራክተሮችን እና 50 ኮምባይነሮችን በሀገር ውስጥ በመገጣጠም ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ከኒው ሆላንድ ጋር ፈጸመ ።

ኩባንያው ከዚህ ቀደም የግብርና ሜካናይዜሽን ለማስፋፋት ሲንቀሳቀስ ቆይተዋል ያሉት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩም ዋና ስራ አስፈጻሚ ሱሌይማን ደደፉ አሁን ከኒው ሆላንድን ጋር ትራክተሮችን በሀገር ውስጥ ለመገጣጠም የተደረሰው ስምምነት የግርብናውን ዘርፍ ለመደገፍ እንደሚያስችል ጠቁመዋል ።
ትራክተሮቹ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ተጠናቀው ለገበያ የሚቀርቡ ሲሆን በተመጣጣኝ ዋጋም ለገበሬው እንደሚቀርቡም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል ።
በ- ሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












