Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ሮዋን ሴባስቲያን አትኪንሰን ሚስተር ቢን

April 4, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | መጋቢት 26፣ 2016| NBC ETHIOPIA-የሳቅ ንጉስ ነው ይሉታል የልጅነት ጊዜያቸውን ያደመቀላቸው፣ ከህጻን እስከ አዋቂ በመላው አለም አድናቂዎች አሉት የሆሊውዱ ፈርጥ በአስቂኝ ድራማዎቹ ዝናን ያተረፈው ሮዋን ሴባስቲያን አትኪንሰን ወይንም ሚስተር ቢን፡፡

ሮዋን አትኪንሰን እንግሊዛዊ ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና  ጸሐፊ ነው፡፡ ነገር ግን ዝናን ያተረፈው ሚስተር ቢን በተሰኘው ተከታታይ አስቂኝ ሲትኮም ላይ ነው።

ሮዋን እ.ኤ.አ ጥር 6 1955 ከአባቱ ኤሪክ አትኪንሰን እና ከእናቱ ኤላ ሜይ የቤቱ አራተኛ ልጅ በመሆን በኒውካስል ታይን፣ እንግሊዝ ተወለደ።

መካክለኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ከሚገኙ የገበሬ ቤተሰብ የተገኘው ሮዋን ከልጅነቱ ጀምሮ ቤተሰቦቹን በስራ በማገዝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቾሪስተር እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን  በሴንት ቢስ ትምህርት ቤት ተከታትሏል።

ቀጥሎም አትኪንሰን በኒውካስል ዩኒቨርሲቲ እና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በኤሌክትሪካል እና በኤሌክትሮኒክ ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።

ሮዋን በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ በነበረበት ወቅት የ5 ደቂቃ ቲያትር ቃል ሳያወጣ በድርጊት ብቻ ታዳሚዎችን ያስጨበጨበ ትወናን በማሳየት ነበር ትወናን የጀመረው።

ከዛም ከኦክስፎርድ ዩንቨርሲቲ በቲያትር የመጀመሪያ ድግሪው በኤሊክትሪካል ኢንጂነሪንግ ደግሞ ማስተርሱን ይዞ ተመርቋል።

እ.ኤ.አ. በ1979 “The Atkinson People” የተሰኘ በ ቢቢሲ 3 የሬዲዮ ጣቢያ ላይ የተላለፈ አስቂኝ ተከታታይ የሬድዮ ድራማ ላይ በመሳተፍ ድብቁን እና እምቁን ችሎታውን ለህዝብ ማሳየት ቻለ።

ሬዲዮ ላይ የጀመረው የሮዋን ጉዞ ወደ ቴሌቭዥን በማደግ እ.ኤ.አ በ 1979 በለንደን ዊኬንድ ቴሌቭዥን ላይ የተላለፈው  Canned Laughter ወይንም የታፈነ ሳቅ የተሰኘ መጠሪያ ባለው አስቂኝ ተከታታይ ድራማ ላይ ለመሳተፍ በቃ።

እ.ኤ.አ በ1986 ለ4 ዓመታት በተላለፈው ብላክ አደር የተሰኘ አስቂኝ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ችሎታውን ማስመስከር ችሏል። በጊዜውም ቢቢሲ ላይ ከተላለፉ እና ስኬታማ መሆን ከቻሉ ሲትኮሞች አንዱ መሆን ችሎ ነበር። ።

ሚስተር ቢን ትምህርቱን ካጠናቀቀ  በኋላ ወደ ጥበብ አፍቃሪያን ለመድረስ በሰአቱ ጊዜ አልፈጀበትም ነበር።ነገር ግን ሚስተር ቢን በህይወቱ የተፈተነበት አንድ ነገር ነበር እሱም ሲያወራ ኮልታፋ መሆኑ ነበር ። ሰዎች ኮልታፋ በመሆኑ እጅጉኑ ይቀልዱበት እና ያሾፉበት ነበር ከዛም አልፎ አትችልም ሲሉም ይተቹት ነበር።

ታዲያ ለዚህ ችግር መፍትሄ በማሰብ ዝምተኛውን ነገር ግን እጅግ አስቂኙን የሚስተር ቢንን ገጸባህሪ መላበስን ያስባል።

እናም  “በእድሜ ትልቅ የሆነ ሰው ነገር ግን በተግባር የትንሽ ልጅ ገጽባህሪ “ያለውን  የሚስተር ቢን ገጽ ባህሪ ይፈጥራል።

እ.ኤ.አ በ 1990 በአስቂኝ ትዕይንቶች የተሞላውን ሚስተር ቢን የተሰኘውን አስቂኝ ተከታታይ ሲትኮም እራሱ በመተውን ለህዝን ማድረስ ቻለ። የሚስተር ቢን ገጽ ባህሪም  በዕለት ተዕለት ተግባራት የሚገጥሙትን የተለያዩ ችግሮችን ለመፍታት ሲሞክር የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቷች የሚያሳይ አስቅኝ ድራማ ነበር።

የገጸ-ባህሪው ራስ ወዳድነት, የልጅነት ስብዕና,እና ከሥነ ምግባር ባህሪው, የፊት ገጽታው እና ከድምጽ አልባ ድርጊቶቹ ጋር ተዳምሮ  ተወዳጅ እንዲሆን አስችሎታል።

ሚስተር ቢን ከሬዲዮ  እና ከቴሌቭዥን ሲትኮሞች በተጨማሪ ወደ ፊልሞች ላይ በመምጣት ጄምስ ቦንድ ፣ ኔቨር ሴይ ኔቨር አጌን፣ ናይጄል ሃውቶርን፣ ላይ በመሪነት በመሳተፍ ድንቅ ችሎታውን አስመስክሯል።

ሚስተር ቢን እ.ኤ.አ. በ1990 የሞንትሬክስ Festival Golden Rose ሽልማት ፣ በ1991 አለም አቀፍ ኤምሚ ምርጥ ታዋቂ የስነጥበብ ፕሮግራም እና በ1994 የአሜሪካ የኬብል Ace ሽልማት አሸንፈዋል።

“ስኬታማ ለመሆን ቆንጆ ፊት እና የጀግንነት አካል አያስፈልግም፣ የሚያስፈልግህ ችሎታ ያለው አእምሮ እና የመስራት ብቃት ነው”። የሮዋን አትኪንሰን ድንቅ የሆነ ንግግር ነው።

በ-ሀይማኖትወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

አጫጭር የሃገር ውስጥ መረጃዎች

Next Post

ቅዱስ ቁርአን ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጥራዝ የተሰበሰበበት አጋጣሚ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ቅዱስ ቁርአን ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጥራዝ የተሰበሰበበት አጋጣሚ

ቅዱስ ቁርአን ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጥራዝ የተሰበሰበበት አጋጣሚ

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሳታፊ ልየታ ስራው ከ70 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሳታፊ ልየታ ስራው ከ70 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ

ጃፓን በሩሲያ ዕቃዎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች

ጃፓን በሩሲያ ዕቃዎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?