አዲስ አበባ | መጋቢት 25፣ 2016| NBC ETHIOPIA-ሀገራት ከተሞቻቸውን በልዩ ልዩ መልኩ በማስዋብ እና አስገራሚ ሰው ሰራሽ ነገሮችን በማላበስ ተመራጭ መዳረሻዎች ማድረጋቸው የተለመደ ነው። አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ያለድካም ተፈጥሮ በለገሰቻቸው ገጸበርከት የቱሪስ ቀልብ ቆንጥጠው ይይዛሉ፡፡
በዓለማችን ልዩ መልከዓምድር የተጎናጸፉና ለአካባቢው መልክ ማድመቂያ ሆነው የዘለቁ እንዲሁም ለሀገራቱ ከፍተኛ ገቢ ከሚያስገኙ ስፍራዎች ለዛሬ ምርጥ 5ቱን እንናስቃኛቹ።
በፊሊፒንስ የሚገኙት የችኮሌት ኮረብታዎች

በአለም ላይ ካሉ ልዩ እና አስገራሚ የተፈጥሮ ቅርፅ ካላቸው አካባቢዎች ውስጥ ይመደባሉ።
በ 50 ስኩር ኪሎ ሜትር ላይ ያረፉት ፣ከ 1ሺ 700 በላይ የሚሆኑ ሚስጥራማ ኮርብታዎች በጎርፍ እና በአፈር መሸርሸር እንደተፈጠሩ ይነገራል፡፡ መጠናቸው ተመሳሳይ መሆኑ ደግሞ ሌላ ልዩነት የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡ በበጋው ወራት ኮረብታዎቹ የተሸፈኑበት ለምለም እፅዋቶች ወድ ቡኒ ቀለም ይቀየራሉ ይህም ክስተት የችኮሌት ኮረብታዎች የሚል ስያሜ እንዲያገኙ እንዳስቻላቸው ይነገራል፡፡ ኮረብቶቹ መች እንደተፈጠሩ ትክክለኛ ግዜው ባይታወቅም 2 ሚሊዮን አመት እንዳስቆጠሩ ተመራማሪዎች ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ባላቸው አስገራሚ የተፈጥሮ አቀማመጥ ዩነስኮ በ አለም ቅርስነት የመዘገባቸው ሲሆን፣ የፊሊፒንስ የጎብኚዎች የመጅመሪያ የመዳረሻ ምርጫቸው ሆነዋል።
የኔቫዳው የፍላይ ጋይሰር ተወርዋሪ ውሃ

ሌላኛው በ እ.ኤ.አ 1916 ሰውች በውሃ ጉድጎድ በቁፋሮ ላይ ሳሉ በደንገት የተፈጠረው እና አስገራሚ የተፈጥሮ መልክ የያዘው የኔቫዳው የፍላይ ጋይሰር ተወርዋሪ ውሃ ነው። ለአይን በሚማርኩ ቀለማት ከማሸብረቁ ባሻገር በበርሃ ውስጥ የተገኘ ተወርዋሪ ውሃ መሆኑ የጎብኚዎችን እና የተፈጥሮ አድናቂዎችን ቀልብ መሳብ ችሏል ። በተለያዩ ግዜያት የውሀው ቀዳዶች መልክና ይዘታቸውን እየቀያየሩ አሁን ላይ ባለ ሶስት ኮረብታ የውሀ መፍለቂያዎች መፍጠር ችለዋል፡፡ ቀዳዶቹ 12 ጫማ ከፍታ ያህል ፍልውሃን ወደላይ ይረጫሉ። ይህም ልዩ ስሜት የሚፈጥር ገጽታ ያለው ሲሆን የቱሪስቶች ቀልብ ማረፊያ ነው፡፡
የዛንጂዳንዣ ብሔራዊ ፓርክ ነው ።

በቻይና የሚገኘው የብሄራዊ ፓርኩ ገጽታ፣ 185 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ የፓርኩ ዋና መስህብ በሚሊዮን በሚቆጠሩ አመታት የተፈጠሩት እና አስገራሚ እይታን የሚፈጥሩት ድንጋይ ምሰሶዎች አቅፎ ይዟል። 650 ጫማ ከፍታ ካለው የድንጋይ ምሰሶ ጀምሮ የተለያየ መጠን ያላቸው አለቶቹ የተለይ ውበትን ሰቶታል። ብርቅዬ የሆኑ የዕፅዋትና የእንስሳት ዝርያዎች መኖሪያ በመሆኑ እና በልዩ ተፈጥሮው ገጽታው በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መዝገብ እንዲሰፍር አስችሎታል፡፡
በፓርኩ ከ 205 ሚሊዮን አመት በፊት እንደበቀሉ የሚነገርላቸው ነጭ አበባ ያላቸው ብርቅዬ ዛፎችን ጨምሮ ወደ 100 የሚጠጉ የተለያዩ ብርቅዬ እንስሳትን ይገኙበታል፡፡
የብሪቲሽ ኮሎምቢአ

ሌላኛው አስገራሚው አቀማመጥ ያለው የተፈጥሮ ሃይቅ ሲሆን የሚገኘውም በብሪቲሽ ኮሎምቢአ ነው ። በአለም ላይ ካሉ በተፈጥሮ መአድናት ከበለጸጉት ሃይቆች አቻ እንደማይገኝለት የሚነገረው ሃይቁ ፣በተለያዩ ትንንሽ ጉድጓዶች የተከፋፈል ነው። በዙሪያው ካሉ ኮረብቶች የሚወረወሩ መዓድናት በጉድጓዶቹ ያለውን ውሀ ቀለም በመቀያየር ማራኪ ውበትን ያላብሱታል። ቀለማቱም በየቀኑ ሊቀያየሩ ይችላሉ። ቦታው ከ ቱሪስት መስበነቱ ባሻገርም በ አካባቢው ላይ የሚገኙ ጎሳዎች ዉሃውን ከበሽታ ለመፈወሻነት እንደሚጠቀሙት እና እንድ ቅዱስ ስፍራ እንደሚቆጥሩት ይነገራል፡፡
የሰሜናዊ አየርላንድ ግዙፍ ቋጥኞች

በሰሜናዊ አየርላንድ አንትሪም ከተማ የሚገኙ ግዙፍ ቋጥኞች፣ ለአካባቢው አይነተኛ መልክ ያጎናጽፋሉ፡፡ ከ60 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በነበረው ጥንታዊ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እንደተፈጠሩ የሚነገርላቸው ስፍራዎቹ ፣ከ40ሺ በላይ ባለ ስድስት ጎን ቋጥኞችን ይዘዋል፡፡ ዩኔስኮ በአለም ቅርስ መዝገብ ያሰፈረው ስፍራው በውስጡ የተለያዩ የአዋፍት ዝርያወችን እና እና በርከት ያሉ እፅዋትንም ይዟል። በአመት በአማካኝ ከ 300ሺ በላይ ጎብኚዎች ወደ ስፍራው ይጎርፋሉ።
በ-የአብስራ ብርሀኑ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












