አዲስ አበባ | መጋቢት 24፣ 2016| NBC ETHIOPIA- በጋና ታዋቂ የ63 ዓመት የባህላዊ ሀይማኖት መሪ የ12 ዓመት ታዳጊ ልጅ በማግባታቸው በሀገሪቱ ትልቅ ቁጣ ቀስቅሷል።
የሀይማኖት መሪው ኑሞ ቦርኬቴ ላዌህ ትሱሩ 33ኛ ቅዳሜ ዕለት በተካሄደ የሠርግ ሥነ-ሥርዓት ነው ታዳጊዋን ያገቡት።
የሰርግ ፕሮግራሙ የሚያሳዩ ቪድዮዎች እና ፎቶዎች እንደሚያሳዩት በርካታ የማህበረሰብ መሪዎች ታድመዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ታዳጊዋ ባሏን በሚማርክ መልኩ እንድትለብስ ሲመክሩ ይደመጣሉ።አክለው የሚስት ተግባራትን ለመከወን እንድትዘጋጅ እና በስጦታ የተሰጣትን ሽቶ ተቀብታ ለባሏ ወሲብ ቀስቃሽ ሆና እንድትገኝ ሲናገሩ ይደመጣሉ።

ቪድዮዎች እና ፎቶዎች ማሕበራዊ ሚድያዎች ላይ በስፋት መሰራጨታቸውን ተከትሎ ጋናዊያን ቁጣቸውን እያሰሙ ሲሆን ንግግሩም በጋናዊያን ዘንድ ያለውን ቁጣ እጅግ ያጋለው ሲሆን ጋብቻው እንዲሁ ለወግ ብቻ የተዘጋጀ አይደለም ማለት ነው የሚል ሐሳብ ጭሯል።
ብዙዎች መንግሥት ጋብቻውን እንዲያፈርስ እና የሀይማኖት መሪው ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ጥያቄ እያቀረቡ ነው።
ታዳጊዋ እና ቄሱ አባል የሆኑበት ኑንጋ የተባለው ጥንታዊ ብሔረሰብ መሪዎች ከተቀረው የጋና ክፍል የቀረበባቸውን ትችት አስተባብለው ትችቱ “ካለማወቅ የመነጨ ነው” ብለዋል።
ታዳጊዋ የቄሱ ሚስት ለመሆን የታጨችው ከ6 ዓመት በፊት መሆኑን ተናግረው ነገር ግን ይህ ከትምህርቷ እንዳላገዳት ይናገራሉ።

ታዳጊዋ ለሁለተኛ ጊዜ በሚካሄድ ሥነ-ሥርዓት የቄሱ ሚስት ለመሆን የሚያስችላት ንፅሕና እንዳላት ይረጋገጣል። ይህ ሥነ-ሥርዓት ልጅ ወልዶ ማሳደግን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትን የምትለማመድበትን ነው ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በጋና ከ18 ዓመት በታች ጋብቻ መፈፀም ሕጋዊ አይደለም ምንም እንኳ በሀገሪቱ ያለዕድሜ ጋብቻ እየቀነሰ ቢመጣም አሁንም በአንዳንድ ሥፍራዎች ይህ ሲከናወን ይታያል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












