፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 20፣ 2016| NBC ETHIOPIA-በየሀገሩ ሰዎች እንደ የአኗኗራቸው ልዩነት የገነቧቸውን ባህሎች፣ ወጎች እና ልዩ ልዩ ልማዳዊ ድርጊቶችን ይንጸባረቃሉ፡፡ ለአንዳንዶች እንደ ባህል የሚወሰዱ እና በማህበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው ድርጊቶች እና እሳቤዎች ለሌሎች እንግዳ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በአለም ዙሪያ እንግዳ የሆኑ ልዩ ልማዳዊ ድርጊቶች መካከል የተወሰኑትን እንንገራችሁ፡፡
1‹‹ሚስትን በከሰል ፍም ላይ ተሸክሞ መራመድ››

ይህ ድርጊት በቻይና በሚኖሩ አንዳንድ ጎሳዎች ዘንድ የተለመደ ሲሆን፣ባሎች ጋብቻ ሲመሰርቱ እንዲሁም ሚስቶቻቸው ማርገዛቸውን ሲያውቁ የሚያደርጉት ነው::
ባል ሚስቱን ተሸክሞ በከሰል ላይ መራመዱ ሚስቱ በወሊድ ግዜ ምጥ እንዳይበዛባት ያደርጋል ተብሎ ይታመናል :: ሌላው በከሰል ላይ መራመድ፣ የተፈጥሮ አደጋዎችን ይከላከላል ተብሎ ይታመናል። ትርዒቱ በርካቶች በአደባባይ ተሰብስበው የሚመለከቱት ነው፡፡
2‹‹ሕፃናትን የመዝለል በዓል››

ይህ በ 1600 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ጅማሮውን እንዳደረገ የሚነገርለት የስፔን ባህላዊ ፌስቲቫል በስፔን ካስትሪሎ ደ ሙርሲያ መንደር በወርሀ ሰኔ የሚደረግ አመታዊ ፌስቲቫል ነው፡፡
በፌስቲቫሉ ሕፃናት በጎዳና ላይ በተነጠፈ ጨርቅ ላይ ከተደረደሩ በኋላ ፣ቢጫ ልብስ የለበሱ እና እንግዳ ጭምብሎችን ያደረጉ ወንዶች ዘለው ይሻገሩዋቸውና ይሮጣሉ፡፡ ከዚያም በህፃናቱ ላይ ሮዝ አበባ ይነሰነስባቸዋል፡፡
የመንደሩ ነዋሪዎች ድርጊቱ ፣ ህጻናቱን ከክፉ መንፈስ እንዲጠበቁ ያደርጋቸዋል የሚል እምነት አላቸው፡፡
3‹‹ለመልካም ዕድል እቃዎችን መሰባባር››

በጀርመን ካሉ የተለያዩ ባህሎች አንዱ ነው ‹‹ፖልቴራባንድ›› ፡፡
ፖልቴራባንድ በቅርቡ የሚጋቡ ጥንዶች ቤተሰቦች እና ጓደኞች እንደ እራት ዕቃዎች እና የአበባ ማስቀመጫዎች ያሉ የሸክላ ዕቃዎችን ለመስበር የሚሰበሰቡበት መደበኛ ያልሆነ ድግስ ነው።
ይህ ባህል ለአዲስ ተጋቢዎች መልካም ዕድል እንደሚያመጣ ይታመናል፡፡ ጥንዶቹ ይበልጡን እንዲፋቀሩ እና እርኩሳን መናፍስት ከዙርያቸው እንዲበሩ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል፡፡
ታዲያ በጀርመን በትዳር ስኬታማ ጥንድ ለመሆን ፣ ከሰርግ ቀን በፊት አህዱ ይህን የእቃ ሰበራ ድግስ ማዘጋጀት ይጠበቃል፡፡
4 ‹‹ለዝንጀሮዎች የሚደረግ ድግስ ››













