፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 20፣ 2016| NBC ETHIOPIA-አማራ ባንክ ከኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ገበያ አክሲዮን ማኅበር የ90 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት ከፍተኛ ባለድርሻ የሚያደርገውን ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራረመ፡፡
አማራ ባንክ የኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ገበያን ለመመስረት የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት መስራች ባለቤት እንዲሆን በተሰጠው ዕድል መሰረት የ10 በመቶ ወይም የ90 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ድርሻ መግዛቱን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋይ ገበያው ጠንካራ ሆኖ እንዲቋቋም እና ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት መወጣት እንዲችል፤ አሰራሩ ቀልጣ ፋ እና ዘመናዊ እንዲሆን ብሎም የታሰበለትን ግብ እና አላማ እንዲያሳካ ባንኩ አቅሙ በፈቀደው መጠን ሁሉ ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም በፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ ተመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ እንቅስቃሴን ለመጀመር የሚያስችል አዋጅ ከፀደቀ በኋላ ወደ ተግባር ለመለወጥ የተለያዩ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በ-ሰብለ ወንድማገኝ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












