አዲስ አበባ | መጋቢት 17፣ 2016| NBC ETHIOPIA- የዓለማችን ከፍተኛ ነዳጅ ሀብት ባለቤት የሆነችው የሳወዲ አረቢያ ንጉስ ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ. ከህዳር 2 ቀን 1964 ጀምሮ እስከ 1975 ህይወታቸውን እስካጡበት እለት ድረስ ሀገሪቷን መርተዋል፡፡ ውልደታቸው እ.ኤ.አ በ1906 ዓ.ም በሪያድ ከተማ ነው፡፡ፈይሰል ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ፡፡
ፈይሰል ከዲፕሎማት እስከ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከሳውዲ አረቢያ ልዑል አልጋ ወራሽ እስከ የሳውዲ አረቢያ ንጉስ በመሆን አገልግለዋል፡፡ የዘመናዊቷ ሳውዲ አረቢያ መስራች የንጉስ አብዱላዚዝ ሶስተኛ ልጅም ነበሩ ፈይሰል።
የንጉሥ ኢብኑ ሳዑድ ልጅ ንጉስ ፋይሰል በ1920ዎቹ እና 30ዎቹ በወታደራዊ ዘመቻዎች ውስጥ ተዋግቷል ዘመናዊ ሳውዲ አረቢያን ለመፍጠር ተጋድሎ ካደረጉ የሀገሪቱ መሪዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በኋላም በተባበሩት መንግስታት የሳውዲ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1934 ሳውዲ አረቢያ በየመን ላይ በከፈተችው ጦርነት ለድሏ ምክንያት ከሆኑ መሪዎች አንዱ መሆናቸውን የህይወታ ታካቸው ያስረዳል፡፡ የአብዱልአዚዝ የበኩር ልጅ ሳውድ ቢን አብዱላዚዝ አል ሳኡድ የአባቱን ህይወት ማለፉን ተከትሎ በ1953 ወደ አባታቸው ዙፋን ላይ ሲነግሱ ፈይሰል ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ በዛው አመት ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ተሾሙ፡፡
ለአስርት አመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሳውዲን የመሩት ፈይሰል እ.ኤ.አ. በ1964 በወቅቱ የሀገሪቱ ንጉስ የነበሩት ሳውድ ቢን አብዱላዚዝ አል ሳኡድ በተደጋጋሚ ሲደረግባቸው በነበረው ጫና ከስልጣናቸውን እንዲለቁ ተገደዱ፡፡ በዚህም ፈይሰል የታላቋን ሳውዲ አረቢያ ንጉስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ሹመት ተሰጣቸው፡፡ ፈይሰል በሀገር ውስጥ እና በሌሎች ሀገራት መሪዎች ዘንድ ተወዳጅ እና በአረቡ አለም ተደማጭነት ያላቸው መሪ ነበሩ፡፡
ሳውዲ አረቢያን ካስተዳደሯት ንጉሰ ነገስታት መካከል ንጉስ ፈይሰል በኢኮኖሚ፣ ትምህርት እና ሀገሪቱን ከማዘመን ጋር በተያያዘ እጅግ ንቁ እና አርቆ አሳቢ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡
ሳውዲ ስትከተል የነበረችው መመሪያዎችን ላይ ስር ነቀል ማሻሻዮችን አድርጓል፡፡ በተለይም የሳውዲ አረቢያን የፋይናንስ ስርአት በማዘመን እና አግሎቶች በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲዳረሱ ለማድረግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

አራምኮ በተሰኘው የሳውዲ አረቢያ ብሄራዊ የነዳጅ ኩባንያ ሀገሪቷ ያላት ከፍተኛ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት በአግባቡ ቁጥጥር እንዲያደርግ የተቋቋመው በንጉስ ፈይሰል የስልጣን ዘመን ነበር፡፡ የእርሳቸው የንግስና ዘመን ሳውዲ አረቢያ በአረቡ እና ሌሎች ሀገራት በቀጠናው ሀያል መሆኗ የታየበት ጭምር ነበር፡፡
የ69 ዓመቱ ንጉስ ፈይሰል ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ፤ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በገዛ የእህታቸው ልጅ መጋቢት 25 ቀን 1975 በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1975 ወንድማቸው ልዑል ካሊድ መንበረ ዙፋኑን ተቆጣጠሩ።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












