፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 17፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ የአፍሪካ በእድሜ ትንሹ ፕሬዝዳንት በመሆን አሸነፉ፡፡
-የጸጥታው ምክር ቤት በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
-የመንግሥታቱ ድርጅት ያጸደቀው የጋዛ የተኩስ አቁም ውሳኔ በተለያዩ ሀገራት መሪዎች ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
-የጸጥታው ምክር ቤት ባስተላለፈው የጋዛ የተኩስ አቁም ውሳኔ አሜሪካ ድምጸ ተአቅቦ አድርጋለች፡፡
-እስራኤል አሜሪካ የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔን አልተቃወመችም በሚል ከአሜሪካ ጋር ልታደርግ የነበረውን ስብሰባ መሰረዟን አስታውቃለች፡፡
-የጃፓን ካቢኔ ሀገሪቱ ያመረተቻቸውን ተዋጊ ጄቶች ለውጭ ሀገራት እንድትሸጥ የሚፈቅድላትን ህግ አጸደቀ፡፡
-በብራዚል በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 27 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












