Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ፋኖስ እና ረመዳን

March 20, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | መጋቢት 11፣ 2016| NBC ETHIOPIA የረመዳን ወር ጾም በዓለም ዙሪያ ባሉ ሙስሊሞች የቀን መቁጠሪያ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ይሰጠዋል፡፡

ይህንን ጊዜ ሊገልጹ የሚችሉ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊና ስነ ጽሁፋዊ ስራዎች በስፋት ይስተዋላሉ፡፡ከነዚህም መካከል የረመዳን ወር ሲነሳ ተያይዘው ከሚታወሱ ነገሮች መካከል አንደኛው ፋኖስ ነው፡፡

ፋኖስ በአሁኑ ጊዜ በመላው አለም በተለይም ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ በረመዳን ጊዜ እንደ ቤት ማስዋቢያነት ያገለግላል፡፡

ከዚህም ባሻገር በዚህ ወቅት በርካታ ቁጥር ያላቸው የስጦታ ካርዶችና ማስታወቂያዎች ላይ የፋኖስን ምስል ማኖር ልምድ ከሆነ ሰነባበቷል፡፡

ፋኖስ ከሌሎች ጊዜያት በተለየ በረመዳን ወቅት የተለየ ቁርኝት ያለው ሲሆን ለዚህም ታሪካዊ ዳራ እንዳለው ይነገራል፡፡

የፋኖስ አመጣጥን የሚያስረዱ የተለያዩ ታሪኮች ቢኖሩም ሁሉም ታሪኮች ግን ወደ ካይሮ የሚያመሩ ናቸው።

ከፋኖስ አመጣጥ ጋር በተያያዘ በስፋት የሚታወቀው ታሪክ የሚጀምረው በ969 ኤዲ ነው፡፡

የወቅቱ በካይሮ ይገኙ የነበሩ ሰዎች የአል ሙኢዝ ሊ-ዲኒ ላህ አል ፋቲ በሌሊት መምጣትን ከመጠባበቅ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

የወቅቱ የሀገሪቱን ገዢ አል ሙኢዝ ሊ-ዲኒ ላህ መምጣትን ተከትሎ ለገዢው ብርሃን በማብራት ያደረጉት አቀባበል ለፋኖስ በመነሻነት የሚቀርብ ስለመሆኑ በርካታ የታሪክ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡

መንገዱን በፋኖሶች ብርሃን ለማድመቅ ህብረተሰቡ ሻማና ፋኖሶችን በመያዝ ማለፊያውን እንዲያበራ ትዕዛዝ ተላልፎለት ነበር፡፡

ከዚያም በዚህም የፋኖሶች ውበትና ብርሃን ድምቀት የተደነቀው አል ሙኢዝ ሊ-ዲኒ ላህ በከተማይቱ ውስጥ ሲዘዋወር ህዝቡ በየምሽቱ ፋኖሶችን እንዲያበሩለት ትእዛዝ ማስተላለፉ ይነገራል፡፡

ሌላኛው ከፋኖስ ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ታሪክ የካይሮ ሰዎች ጨረቃን ለማየት ሞካታም ወደ ተባለ ኮረብታ ገዥያቸውን ከመሸኘት ጋር የተቆራኘ ስለ መሆኑ የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡

በአሮጌ የካይሮ መግቢያ በሮች ማለትም ባብ ኤል-ናስር ባብ ኢል-ፈቱህ እና ባብ ኤል-ዳሃብ አልፈው በመንገድ ላይ ህጻናት ፋኖሶችን ይዘው የረመዳንን ወር መግቢያ ይጠባበቁ ነበር፡፡

ከነዚህ የመነሻ ታሪኮች ባሻገር የፋኖሶቹ ታሪክ የሚጀምረው በ10 ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ የሚናገሩ የታሪክ ሰዎችም አሉ፡፡

በወቅቱ የነበረው ሀገረ ገዥ ሴቶች ዓመቱን ሙሉ ቤታቸውን ለቀው እንዳይወጡ ክልከላ አደረገ፡፡

ይህ በሴቶች ላይ የተጣለው ክልከላ ታዲያ ፀሀይ ከጠለቀች በኋላ ለሶላት መስጅድ እንድትገኝና ዘመዶቿን ብሎም ጎረቤቶቿን እንድትጎበኝ በረመዷን ወር ተነሳ፡፡

ይህ እግድ ይነሳ እንጂ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠው ፋኖስ ነበር፡፡ማንኛዋም ሴት በምሽት መንቀሳቀስ የምትችለው መንገዳቸውን ለማብራትና አንዲት ሴት በዛ መንገድ እያለፈች መሆኑን ለወንዶች ለማሳወቅ ፋኖሶችን በያዙ ወንዶች ልጆች ታጅባ ሊሆን እንደሚገባ ታወጀ፡፡

Ramadan Lanterns on display welcoming the holy month of Ramadan

ከጊዜ በኋላም የግብፅ ፋኖሶች በየአካባቢው ተሰራጭተው በሌሎች በርካታ ከተሞች የረመዳን ባህል ሆነዋል።በተለይም ደግሞ በደማስቆ፣ አሌፖና ኢየሩሳሌም በስፋት አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡

በወቅቱ በፋኖሶች ውበት የተገረመው የሀገሪቱ ገዥ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን በንግድ ስራ እንዲሰሩ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን ከዚህም ባሻገር ሰዎች በሮቻቸው ላይ መብራቶችን እንዲሰቅሉ የሚያስገድድ አውጆም ነበር፡፡

በዚህ ምክንያት የፋኖሶች ኢንዱስትሪ እያደገ ሄዶ ፋኖሶች በሁሉም ቅርጾች፣ ቀለሞችና መጠኖች በስፋት መመረት ጀመሩ፡፡

በአሁኑ ወቅት በስፋት የሚመረቱት ዘመናዊዎቹ ፋኖስ ከረመዳን ጋር ቁርኝት ካላቸውና እንደ ጨረቃና ኮከብ ሁሉ መገለጫ ለመሆን ችሏል፡፡

በተከበረው የረመዳን ወርም በርካቶች ቤታቸውን በቀለማት ባሸበረቁ ፋኖስዎች ያበራሉ።

ShareTweetShare
Previous Post

አጫጭር የውጭ መረጃዎች

Next Post

ክሎፕ ቶማስ ቱኽልን ለመተካት በአማራጭነት አልተካተቱም

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
6
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
6
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
14
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
36
Next Post
ክሎፕ ቶማስ ቱኽልን ለመተካት በአማራጭነት አልተካተቱም

ክሎፕ ቶማስ ቱኽልን ለመተካት በአማራጭነት አልተካተቱም

ኢትዮጵያ በእርምጃ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

ኢትዮጵያ በእርምጃ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

አጫጭር የሀገር ውስጥ መረጃዎች

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?