እግር መንገድን የሁልጌዜ ልማድ ማድረግ ብዙ አካላዊ እና አእምሮአዊ ጠቀሜታዎች አሉት።
-ልባችን እንዲጎለብት እና የደም ግፊት መጠናችን እንዲቀንስ ይረዳናል
-የልብ ህመም እና የስትሮክ አደጋን ይከላከላል
-ክብደታችን እንዲቀንስ እና የተስተካከለ የሰዉነት አቋም እንዲኖረን ይረዳል
-የጉልበት እና የንቃት መጠናችን እንዲጨምር ያደርጋል
-ጡንቻ እንዲጠነክር እና መገጣጠሚያዎች በቀላሉ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ያደርጋል
-የጭንቀት መጠን እንዲቀንስ እና ከድባቴ ለመላቀቅ ይረዳል
-የማስታወስ ችሎታ እንዲሻሻል ይረዳናል
ስራ ላይ የበለጠ ማተኮር እንዲቻል ያግዛል
-የፈጠራ ችሎታን እንዲመጨመር ይረዳል
የእግር መንገድን የሁልጊዜ ልማድ እንድናደርግ:-
1. በትንሹ መጀመር፤ በቀን ለ 10 ደቂቃ ያህል መራመድ ከዛም ቀስ በቀስ የምንራመድበትን ርቀት መጨመር
2. አቅራቢያችን ያለ ቦታ ለመሄድ ከፈለግን ታክሲ ከመጠቀም ይልቅ በእግር መሄድ ወይም ሊፍት ከመጠቀም ይልቅ በደረጃ መውጣት ፤ መኪና ካለን ደሞ መኪናችንን ራቅ አድርጎ በማቆም ያንን ርቀት መራመድ
3. በምንራመድበት ጊዜ ሬዲዮ ማዳመጥ
4. ቤተሰቦቻችንን፣ ጓደኞቻችንን ወይም የትዳር አጋራችንን አብረውን እንዲራመዱ መጋበዝ ናቸው።












