፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 06፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ከ3.7 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ ኮምፖነንት 3.2 የተሰኘ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተካሄደ፡፡
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ በዓለም ባንክና በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ለቤት ውስጥ፣ ለንግድ እና ለማህበራዊ አገልግሎት ከተማን ጨምሮ የኤሌክትሪክ መስመር ባልተዳረሰባቸው የገጠር አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የተቀናጀ አሰራር የሚተገበር ስለመሆኑ የተነገረው ፕሮጀክቱ
እ.ኤ.አ አቆጣጠር ከ2021 ጀምሮ ሲተገበር የቆየው ያልተማከለ የኤሌክትሪክ ኃይልና መብራት አቅርቦት ፕሮጀክት አካል መሆኑም ተመላክቷል።
በ-ሀይማኖት ወርቁ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












