፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መጋቢት 05፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፓስፖርትን ለማግኘት ዜጎች እንግልት እንዳለባቸው በተደጋጋሚ ሲነሳ መቆየቱ ይታወቃል።
የኢምግሬሽንናዜግነት አገልግሎት የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የኢምግሬሽንናዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በመዲናዋ ብሎም በመላ አገሪቱ እየታየ ያለው ፓስፖርት ለማግኘት ያለው ጭንቅንቅ የአመራር ለውጥ ከመደረጉ በፊት የተጠራቀመ የፓስፖርት ፍላጎት መኖር እንዲሁም ከ30ሺህ የማይበልጥ የታተመ ፓስፖርት መገኘቱ እንደምክንያት አንስተዋል።
ይህን ለማስተካከልም በተሰራ ስራ በዚህ 6 ወር ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት ወደ ሀገር ውስጥ እንደገቡ እና ከ640 ሺህ በላይ ፓስፖርት ፈላጊዎች አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል።
በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያም በቅንጅት የሚሰራው የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በአሰራር ዙሪያ ክፍተት መሰተዋሉን አስመልከተው ምላሽ የሰጡት ዋና ዳይሬክተሯ ቪዛ፣ፖስፖርት እና ዶክመንቶችን ለማጣራት ተቋሙ በሚያደርገው አሰራር መረጃ ያላሟሉትን በመለየት ሂደት ብልሹ አሰራር የፈፀሙ ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት 205 ከውጭ አገር ደላሎች ጋር ተመሳጥረው በህገወጥ ተግባር ተሰማርተው የተገኙ የአገልግሎቱ ሰራተኞች ከስራ እስከማባረር የደረሰ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተብሏል፡፡
የኦላይን አሰራሩንም በማቀላጠፍ ከመጋቢት 16 ጀምሮ ለቀጠሮ ሁለት ወር እንደሚወስድ ተገልጿል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












