አዲስ አበባ | የካቲት 27፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የታላቁ የህዳሴ ግንባታ የተጀመረበት 13ተኛ አመት በማስመልከት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት መግለጫ ተሰጥቷል ። በመግለጫው የግድብ 13ኛ አመትን ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጿል ።


መሰረት ድንጋይ የተቀመጠበትን ቀን በተለያዩ ሁነቶች በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ኮሚቴ ተቋቁሞ ትልቅ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን የቦንድ ማሰባሰብ ሳምንት ፣የስዕል አውደርእይ ፣የፓናል ውይይት እንዲሁም ኤግዚቢሽን እንደሚኖር ተጠቁሟል ።
13ኛ አመት በተለያዩ ሁነቶች በደመቀ ሁኔታ ሲከበር ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እውቅና በመስጠትና ድጋፎች ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ሁኔታ እንደሆነ ተገልጿል ።
በዚህ ፕሮግራም 300 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ተገልጿል ። በአሁኑ ሰአት የግድቡ አጠቃላይ ግንባታው 95 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን 98.9የሲቪል ስራው መጠናቀቁም ተመላክቷል።
በ- ሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












