አዲስ አበባ | የካቲት 27፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የሀይቲ ጋንግ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪየል ሄነሪ ከስልጣን ካልወረዱ በሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ይነሳል ማለቱ ተገለጸ ፡፡ ከሰሞኑ በሀይቲ የታጠቁ ቡድኖች የተቀናጀ ዘመቻ በመጀመራቸው በሀገሪቱ ከፍተኛ ሽብር መናሰቱ የሚታወቅ ሲሆን ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መኖሪያቸውን እየለቀቁ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የሀይቲ ጋንግ መሪ ጂሜ ቸርዚየር እንደገለጸው በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሄነሪ ስልጣናቸውን ካልቀቁ ዘር ማጥፋት የሚያስከትል ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል ፡፡ ዘገባው አልጀዚራ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












