አዲስ አበባ | የካቲት 20፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ኢትዮጵያ ወራሪዋ ጣሊያንን ድል የነሳችበት የአድዋ ድል ኢትዮጵያን ስጋና ደም ያለበሰ ከመሆኑም በተጨማሪ የአለምን ታሪክ የቀየረ ነው::


የሁለተኛው ምዕራፍ ሁለተኛው የሐሳብ መዋጮ መድረክ “አድዋ የኢትዮጵዊነት ድል አፍሪካዊ አርማ የትውልድ ውርስ” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ይገኛል::
በመድረኩ የአድዋ ድል ጥቁሮች ማሸነፍ ነጮችም መሸነፍ እንደሚችሉ ያሳየ በመሆኑ በወቅቱ በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ አፍሪካውያንን ለድል ያነሳሳ እንደሆነ ተጠቅሷል::
ከዚህም በተጨማሪ ከድሉ ማግስት የኢትዮጵያን ተደማጭነት የዲፕሎማሲ አቅሟን ያሳደገ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅናዋ ከፍ እንዲል ማድረጉ ተነስቷል::
በሐሳብ መዋጮ መድረኩ ላይ አባት አርበኞችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን በታሪክ ተመራማሪዎች የመነሻ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል::
በ-አክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












