፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
አዲስ አበባ | የካቲት 20፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት 128ኛው የዓድዋ ድል የአባቶቻችን ጀግንነትን በሚመጥንና የሰራዊቱን አኩሪ ድል በሚያጎላ መልኩ ይከበራል ብሏል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በመከላከያ ሚኒስቴር የበላይ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እና በመላው ሀገሪቱ በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡
በዓሉ የሀገር ፍቅር ስሜትን በሚያንፀባርቅ መልኩ ለሀገር መስዋዕትነት የተከፈለውን ድል ባከበረ መልኩ ይከበራል ብለዋል፡፡
የዓድዋ ድል በአዲስ አበባ በቅርቡ በተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዕለቱን በሚያሳዩ በተለያዩ ታሪካዊ ፣ወታደራዊ እና ጥበባዊ ትዕንቶችን የሚከበር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ሌላው በመግለጫው ከተነሱ ጉዳዩች በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የተከሰቱ ሰሞነኛ የትራፊክ አደጋዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆናቸው ትኩረት ይፈልጋል ተብሏል፡፡
መንግስት የተለያዩ ስራዎችን በትራፊክ ዙሪያ እያከናወነ ቢሆንም የአደጋዎች ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በመሆኑ ለጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት በአገር አቀፍ ደረጃ በተከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች የ1 ሺህ 358 ዜጎች ህይወት ማለፉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ ገልፀዋል፡፡
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv


See insights and ads
Like
Comment
Share












