አዲስ አበባ | የካቲት 14፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በቬንዙላ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በደረሰ የመሬት መደርመስ 23 ሰዎች ሞተዋል ተባለ፡፡ በማዕድን ማውጫ ቦታው ወደ 200 ሰዎች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

በቦሊቫ ግዛት በህገወጥ መንገድ ማዕድን ሲያወጡ የነበሩ የአደጋው ሰለባ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፤ ቡላ ሎካ ተብሎ በሚታወቀው የቦሊቫ ጫካ ውስጥ በሚገኘው የማዕድን ማውጫ ብዛት ያላቸው ሰራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












