አዲስ አበባ | የካቲት 12፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ለተወጣጡ ሴት አመራሮች እና ሰራተኞች የማህፀን በር እና የጡት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሁም የቅድመ ምርመራ መርሀግብር አካሂዷል።


በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ የሆነውን የማህፀን በር እና የጡት ካንሰር በሽታን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ቅድመ ምርመራሮችን ማከናወን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መድረኩ መዘጋጀቱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ተሳትፎ እና ማብቃት ዳይሬክተር ስፍራሽ አልማው ገልፀዋል።
በእለቱ ከ750 በላይ ሴቶች በማህፀን ጫፍ እና የጡት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ቅድመ ምርመራ መርሀ-ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።

ከ530ሺ በላይ አዳዲስ የማህፀን በር ካንሰር ኬዝ በየዓመቱ በመላው ዓለም የሚከሰት ሲሆን እ.ኤ.አ በ2022 በኢትዮጵያ በተደረገ ጥናት ከ5ሺ በላይ ሴቶች ህይወታቸው አጥተዋል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












