አዲስ አበባ | የካቲት 12፣ 2016| NBC ETHIOPIA -በዛሬው ዕለት ታሪክ ሲወሳ ከሰማንያ ሰባት ዓመታት በፊት፣የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን በፋሺስት ጣሊያን በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን ነው፡፡
ፋሽስት ጣሊያን የአድዋ ሽንፈቱን ለመበቀል ከአርባ ዓመት ዝግጅት በኋላ ዳግም ኢትዮጵያን በመውረር ሕዝቡን ቁም ስቅል በሚያሳይበት ወቅት የካቲት 12/ 1929 አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በጦር አዛዡ ሩዶልፍ ግራዚያኒ ላይ ቦምብ ወርውረው ጉዳት ማድረሳቸውን ተከትሎ የጣሊያን ጦር ከ30 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በግፍ መጨፍጨፉን ታሪክ ይዘክራል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv