አዲስ አበባ | የካቲት 08፣ 2016| NBC ETHIOPIA – የጤና መረጃና ምክክር አገልግሎት መስጫ 952 ነፃ የስልክ መስመር የንቅናቄ መድረክ የ20ኛ ዓመት ምስረታን አስመልክቶ የጤና ሚኒሰቴር አገልግሎቱን ይበልጥ ለማስተዋወቅና ለመገምገም እንዲቻል በአዳማ ከተማ የዉይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

የጤና መረጃና ምክክር አገልግሎት መስጫ መስመሩ በአመት ከ130ሺ በላይ ጥሪዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ከ5 ሚሊየን በላይ አጭር የፅሁፍ መልዕክትም ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንደሚያደርግ አስታዉቋል ።
በይበልጥ ደግሞ በእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት፣ በአይምሮ ጤና፣በወጣቶች ስነ-ተዋልዶ ጤና እና በሱስ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ያለ ምንም ክፍያ ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ብቁ ባለሙያዎችን አደራጅቶ እንደሚሰራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።
በ-ማህሌት ግርማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv