አዲስ አበባ | የካቲት 07፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ግብጽና ቱርክ ጠንካራ ሆነ የስትራቴጅክ አጋርነት ለመመስረት መስማማታቸው ተገለጸ፡፡
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በካይሮ ባደረጉት ስብበሰባ በጋራ ተጠቃሚነትና ከፍ ያለ የስትራቴጅካዊ ትብብር ለመገንባት ያለመ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው የተፈራረሙት ተብሏል ፡፡
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲና የቱርኩ አቻቸው ኤርዶጋን የሁለቱን ሀገራት ፖለቲካዊ፤ ብሄራዊ ደህንነት ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ትስስርን ለማዳበር በማሰብ የጋራ ስምምነት ሰነድ እንደተፈራረሙ ታውቋል፡፡ ዘገባው የቲ አር ቲ ወርልድ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv