አዲስ አበባ | የካቲት 04፣ 2016| NBC ETHIOPIA -የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመጀመሪያውን ምዕራፍ አጠናቆ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በሰጠው መግለጫ፤ እስካሁን በተሰራው ስራ የተሳታፊዎች ልየታን ጨምሮ ለምክክሩ ሂደት ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጿል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አረአያ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች 1 ሺህ 400 ወረዳዎችን ያካለለ ውይይቶች መደረጉን አንስተዋል።
በትግራይ ክልል እና በአማራ እንዲሁም በኦሮሚያ ጥቂት ቦታዎች የቀሩ ስራዎች በቀጣይ ይጠናቀቃሉ ብለዋል።
በቀጣይ ምዕራፍም በክልሎች፣ በፌዴራል ደረጃ እና በውጭ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች አጀንዳ የመሰብሰብ ስራ እንደሚሰራም ተመላክቷል።
አጀንዳ መሰብሰብ ከተጠናቀቀ በኋላ አጀንዳዎች ሁሉ ወደ ዋናው ፅህፈት ቤት ገብተዉ የአጀንዳ መረጣ ይደረጋል ተብሏል። የአጀንዳ መረጣው ሲያበቃ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮችን ወደ ፊት በማምጣት ምክክር ወደ ማድረግ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አስታዉቋል።
በሂደቱ ሁሉንም አካል አሳታፊና አካታች የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዓረአያ ተናግረዋል።
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ 8112 ነፃ የስልክ ጥሪ እና አጭር የጽሑፍ መልዕክት መቀበያ አገልግሎት ማዕከል ወደ ስራ ማስገባቱንም ይፋ አድርጓል።
በ-ሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












