አዲስ አበባ | የካቲት 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ከሀገራችን ህዝብ 1.6 በመቶ የሚሆነው ማለትም ወደ 6 ሚሊዮን የሚጠጋው ማህበረሰብ የሚጥል ህመም ታማሚ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በሀገራችን ስለ ህመሙ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆን በሽታው እንዲስፋፋም ምክንያት መሆኑ ይነሳል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው አነሳ ግንዛቤ ለመቀየር የጤና ሚኒስቴር በየአመቱ የሚጥል ህመም ሳምንት በማዘጋጀት ስለ ህመሙ መረጃዎች ለማህበረሰቡ ለመስጠት እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
ዘንድሮም የጤና ሚኒስቴር ከኬርኢፒለፕሲ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር 9ኛው ብሄራዊ የሚጥል ህመም ሳምንት ከየካቲት4 እሰከ 17 በተለያዩ ሁነቶች እንደሚከናወን አስታውቋል፡፡
በመርሃ ግብሩም በተመረጡ ትምህርት ቤቶች እና ጤና ጣቢያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣል ተብሏል፡፡ ከእዚህም ባሻገር ከክልል እና ከከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና እንደሚሰጥ ተጠቁማል፡፡
በሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












