አዲስ አበባ | የካቲት 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ሱዳናውያን ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ በቱኒዚያ ባህር ዳርቻ ሰጥማ ቢያንስ 13ቱ ህይወታቸውን ሲያጡ 27 ሰዎች መጥፋታቸውን የቱኒዚያ ባለሥልጣን ተናገሩ።
በጀልባዋ ላይ ተሳፍረው ከነበሩት ከ40 በላይ ስደተኞች በሕይወት የተገኙት ሁለት ሰዎች ብቻ ሲሆኑ የጠፉት እየተፈለጉ መሆኑን ባለሥልጣኑ ገልጸዋል።
አደጋው የደረሰው ጀልባዋ ከስፋክስ ከተማ አቅራቢያ ከምትገኝ ጀቢኒያና ከተባለች አነስተኛ መንደር ተነስታ እየተጓዘች ሳለ ነበር።
በቱኒዚያ የሞናስቲር ከተማ የፍትሕ ቢሮ ቃል አቀባይ ፋሪድ ቢን ጂሃ የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












