-አዲስ አበባ | ጥር 30፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በንፁህ የመጠጥ ውሃ ዙሪያ በዘርፉ ከተሰማሩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚመክር መድረክ እያካሄደ ነው።

በመርሃግብሩ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽነት እንደሀገር እየጨመረ መሆኑን አንስተው፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በየአገሪቷ ያለውን ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማስፋፋት በሚሰሩበት ወቅት የሚታየውን ችግር ለመረዳት እና ለቀጣይም አቅጣጫ ለማስቀመጥ የተዘጋጀው መድረክ እንደሚረዳ ጠቁመዋል።
በመርሀግብሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በማህበረሰብ ተኮር የተሰሩ ስራዎች ያጋጠሙ ችግሮች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












