አዲስ አበባ | ጥር 30፤ 2016| NBC ETHIOPIA -15ኛዉ ከተማ አቀፍ የባህል ፌስቲቫል በተለያየ መልኩ ሲከበር መቆየቱ ይታወቃል። ይህንኑ ፌስቲቫል በተመለከተ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቶክ ሾዉ መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

“ባህሎቻችን ማወቅ ስብራቶቻችንን መጠገን” በሚል ሃሳብ ሲካሄድ የቆየዉ የባህል ፌስቲቫል ባህልን ከማስተዋወቅ ባለፈ ያሉንን ሀብቶች በኢኮኖሚዉ ዘርፍ ለመጠቀም ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረገ ተገልጿል።
ሰዎች ለአንድ ሀገር ያላቸዉ ዕይታ ለቱሪዝም ሴክተሩ ወሳኝ ነዉና የሀገር ገፅታን በመገንባት ረገድ ያሉንን ሀብቶችና ቱዉፊቶች በአግባቡ መጠቀም በገፅታ ግንባታ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸዉ ተብሏል።
በቶክ ሾዉ መድረክ ላይ ዕደ ጥበባት ለኢኮኖሚዉ ዘርፍ ከቱሪዝምና ከሀገር ገፅታ ግንባታ እንዲሁም ከስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር ያላቸዉ ፋይዳ ከፍተኛ ስለመሆኑ ተነስቷል።
በተጨማሪም በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶችና በቀጣይም ምን መሰራት አለበት የሚሉ ሀሳቦች ላይ ዉይይት በመደረግ ላይ ይገኛል።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












