አዲስ አበባ | ጥር 28፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ እየተደረገ ባለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ባሉበት ወቅት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው “ኦነግ ሸኔ እያደረገው ያለው ልማት እንዳይሰራ ማስተጓጎል እንዲሁም ንብረት ማውደም በመሆኑ ይህ ጥፋት ነው፤ የገደልከውን እና ያገትከውን ህዝብ ልምራ ማለት አግባብነት የለውም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።
ከኦነግ ሸኔ ጋር ሲደረግ የነበረዉ ድርድር በስምምነት ያልተሳካበትን ምክንያት የተጠየቁት ዐቢይ አህመድ፤
ይሄነው የሚባል የድምዳሜ ሀሳብ ላይ ባለመድረሱ ምንም ማሳወቅ እንዳልተቻለ እና በተደረገላቸው የሰላም ጥሪ መሰረት የሀሳብ ትግል ለማድረግ ባለመቻላቸው ነው ብለዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












