አዲስ አበባ | ጥር 24፤ 2016| NBC ETHIOPIA-15ው ከተማ አቀፍ የባህል ፌስቲቫል ‹‹ባህሎቻችንን ማወቅ፤ስብራቶቻችንን መጠገን›› በሚል መሪ ቃል መካሄድ ጀምሯል።

በፌስቲቫሉ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳና የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
ዘመናዊነትን ተከትሎ በርካታ ባህላዊ እሴቶቻችን እየጠፉ ነው ያሉት አዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው በመጥፋት ላይ ያሉትን መልካም እሴቶች ለማወቅ ብሎም ለሌሎች ለማስተዋወቅ ፌስቲቫሉ ጠቀሜታ እንደለው ገልጸዋል ። የቢሮ ኃላፊዋ አክለው ፌስቲቫሉ የባህል ልውውጥ የሚካሄደው በመሆኑ ሁሉም የከተማዋ ማህበረሰብ በፌስቲቫሉ ላይ እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።
ጊዜን ቦታን ሳንጠብቅ መሰል ፌስቲቫሎችን በማከናወን የባህል ስብራቶቻችን መጠገን ብሎም የሀገሪቱን እምቅ ባህሎች በማስጠበቅ ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ ተናግረዋል።
ባህሎቻች ድንበር ተሻጋሪ ለማድግ እንዲሁም ወደ ቱሪዝም ሀብት በመቀየር ረገድ ገና ብዙ ስራ ይቀረናል ያሉት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ባህሎቻችን ለኢኮኖሚ ካለው አስተዋጽኦ አንጻር በርካታ ስረሰዎች መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል ። ከተማ አስተዳደሩም መሰል የባህል የፌስቲቫሎች በቀጣይ ለማከናወን እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
ፌስቲቫሉ ለሶስት ቀናት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን የሃገራችን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የባህል መንደር ምስረታን ጨምሮ የአኗኗር ዘዴ፣ ኃይማኖታዊ ስርዓቶች፣ የሃገረሰባዊ ምግቦችና መጠጦች አዘገጃጀት እንዲሁም የተለያዩ ሃገርኛና ባህላዊ ክዋኔዎች እየቀረቡበት ነው።
በሰላማዊት ወ/ገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












