– አዲስ አበባ | ጥር 24፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ግዙፏ የኢትዮጵያ መርከብ ዓባይ ፪ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ጭነት ይዛ ጅቡቲ መድረሷን አስታውቋል፡፡
-አለም ዓቀፉ የመኪና አምራች ሚትስቡሺ በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና በትሬዲንግ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመጠቀም ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።
-የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ነጻ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን በነጻ የሚሰጡት አገልግሎቶችም የሕጻናት ህክምና፣ የውስጥ ደዌ ፣ የጥርስ ፣ የልብ ፣ የቆዳና አባላዘር እንዲሁም የፕላስቲክ ቀዶ – ሕክምና መሆናቸው አስታውቋል፡፡
-ከ70 በላይ በቤት ልማት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተቋማት የሚሳተፉበት ‘‘አርኪ ሆምስ ኤክስፖ” ከየካቲት 15- 17 በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












