አዲስ አበባ | ጥር 23፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ጊፍት ሪልስቴት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 4 በዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ ዜጎች ያስገነባዉን ዘመናዊ G+4 ህንፃ የምረቃ ስነ-ስርዐት በማከናወን ላይ ይገኛል።


አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ በምረቃ ስነስርዓት ተገልጿል።
በክፍለከተማዉ የኢኮኖሚ ሁኔታቸዉ ሳይሟላ በችግር የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ችግር ለመፍታት በሚል ለ30 አባወራዎች የመኖሪያ ቤቶች የተላለፉ ሲሆን በዚህም የአባወራዎቹን የቤትን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ ተችሏል ተብሏል።
በመኖሪያ ግንባታ ላይ ከተሰማራ ከ20 አመታት በላይ ያስቆጠረዉ ጊፍት ሪልስቴት ቁሳዊ አሻራን አኑሮ ከማለፍ ባሻገር ህብረተሰብን መገንባት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ሲሉ የጊፍት ሪልስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ ተናግረዋል።
315 ቤቶችን በግማሽ አመት በማጠናቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፍ ያደረገዉ ክፍለከተማዉ በቀጣይም ከከተማ አስተዳደሩና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ቀጣይ ስራዎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ እንደሚሰራ ገልጿል።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












