አዲስ አበባ | ጥር 23፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በተለያዩ ጊዜያት ሲራዘም የቆየው የህዝብና ቤት ቆጠራ በ2018 ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል::

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ቆጠራው እንዲራዘም ምክንያት መሆኑን ጠቁመው በ2018 የሚካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ በቴክኖሎጂ የታገዘ ይሆናል ነው ያሉት::
ከ2016 ጀምሮ እስከ 2018 የሚተገበር የኢትዮጵያ ስታቲስቲካል ልማት ፕሮግራም የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል::
ይህም ፕሮግራም በተለያዩ ዘርፎች ያሉትን ሀገራዊ ወቅታዊ መረጃዎች ለመገንዘብ እንደሚረዳ ተመላክቷል::
በአክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












