አዲስ አበባ | ጥር 22፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የአዲስ አበባ ባህል፣ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ “ባህሎቻችንን ማወቅ ስብራቶቻችን መጠገን” በሚል መሪ ቃል ከጥር 24-26 በጊዮን ሆቴል የባህል ፌስቲቫል ሊያካሄድ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የከተማውና የአካባቢው ነዋሪዎችን ተሳታፊ እንደሚያደርግ የተገለፀ ሲሆን በዋናነትም የማህበረሰቡን ወግ፣ ማህበራዊ እሴቶች፣ የህይወት ፍልስፍናዎቹን ፣ ልምዱንና መስተጋብሩን በሚያሳዩ የባህል ክዋኔዎችና የእደ-ጥበብ ፈጠራ ምርቶችን በማጎልበት የገበያ ትስስርሮችን በመፍጠር ከዘርፉ የሚገኘውን ማህበራዊ መስተጋብር፣ ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታና ፋይዳዎችን ማስገኘት ነው፡፡
በፌስቲቫሉ ላይ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የአኗኗር ዘዴ፣ የቁሳዊና መንፈሳዊ ድርጊቶች ፣ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ፣ የሀገራዊ ምግብና መጠጦች አዘገጃጀቶች እንደሚካሄድም ተጠቅሷል፡፡
በማህሌት ግርማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












