አዲስ አበባ | ጥር 21፤ 2016| NBC ETHIOPIA -ቢሊየነሩ ኢላን መስክ፤ ኒውራሊንክ በተባለው ኩባንያው ሰዎች አንጎል ውስጥ የሚገጠም ገመድ አልባ ቺፕ መሥራቱን ይፋ አድርጓል።

ይህ ቺፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ላይ መኩራ የተደረገበት ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ውጤቶች እንደሚያሳዩት የኒውሮን መጠንን እና የነርቭ ‘ኢምፐልስ’ ከፍ ማለት የተስተዋለ ሲሆን ታካሚው እያገገመ ይገኛል።
የኩባንያው ዓላማ የሰው ልጅን አእምሮ ከኮምፒውተር ማስተሳሰር ሲሆን ሌሎች ተመሳሳይ ምርት የሚያመርቱ ድርጅቶችም ይህን ቺፕ የሰው ልጆች አንጎል ውስጥ መግጠም ጀምረዋል።
ኢላን መስክ ከምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን (ኤፍዲኤ) ቴክኖሎጂውን ሰዎች ላይ እንዲሞክር ይሁንታ የሰጠው ባለፈው ግንቦት ነው ፤ከዚያ ቀደም ሌሎች ኩባንያዎች ይህን ፈቃድ ለማግኘት ብዙ ቢጥሩም አልተሳካላቸውም ነበር።
ለዚህ ሥራ የተመደበው ሮቦት 64 ከፀጉር ዘለላ የቀጠኑ ገመዶችን ጭንቅላት ውስጥ በመግጠም “የእንቅስቃሴ ሂደትን” መቀጣጠር ይጀምራል።እኒዚህ ቀጫጭን ዘለላዎች ቻርጅ የሚደረጉት ገመድ አልባ በሆነ ቴክኖሎጂ ነው።
64ቱ ዘለላዎች ምንም ገመድ ሳይጠቀሙ የአእምሮ የሚገኙ መረጃዎችን (ሲግናል) ወደ አንድ መተግበሪያ ይልካሉ። መተግበሪያው ደግሞ አንድ ሰው ምን ዓይነት እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዳሰበ መረዳት ይችላል።
ኢላን መስክ በቀድሞው ስሙ ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ማህበራዊ ድህረ ገፁ ላይ ባሰፈረ መልዕክት፣ አዲሱ ቴክኖሎጂ መጠሪያው ቴሌፓቲ እንደሚባል እና ይህን ቴክኖሎጂ መጀመሪያ መጠቀም የሚችሉት እጅ እና እግራቸውን ያጡ ሰዎች ናቸው ሲል ጨምሮ ተናግሯል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












